በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

    የባለስልጣኑ ራዕይ፡-

                በ2022 በአገር አቀፍ ደረጃ ብቁ እና ተወዳዳሪ ተቋማትና ባለሙያ ተፈጥሮ ማየት፤

   የባለስልጣኑ ተልዕኮ፡-

               በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ተቋማትን ጥራት፣ ተገቢነትና በኢንዱስትሪው መሪነት የባለሙያዎች የሙያ ብቃት በምዘና በማረጋገጥ ደረጃውን
               የጠበቀ ብቁና ተወዳዳሪ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም እና ባለሙያ መፈጠሩን ማረጋገጥ ነው፡፡

  የባለስልጣኑ እሴቶች፡- 

    • ለትምህርትና ስልጠና ጥራት ቅድሚያ መስጠት
    • ሙያ ስነምግባር
    • የላቀ ምዘና
    • በጋራ መስራት
    • በዕውቀትና በእምነት መስራት
    • ተጠያቂነት
    • ለህግ መገዛት
    • የላቀ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት

     የባለስልጣኑ ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች፡-

    • የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ጥራትና ተገቢነት
    • የላቀ የሙያ ብቃት ምዘና   

 

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ  አዋጅ ቁጥር 64/ 2011 መሰረት የሚከተሉት ሥልጣን፣ ተግባርና ሃላፊነት ተሰጥቷል፤
  1. በአጠቃላይ ትምህርት እና በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሠጥ ትምህርትና ስልጠና ከሀገሪቱና ከከተማ አስተዳደሩ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፍላጎትና አግባብነት ካላቸው ሥርዓተ ትምህርት፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጋር መገናዘባቸውን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል አስፈላጊ እርምጃዎችን ይወስዳል፤
  2. አጠቃላይ የትምህርትና በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በህግ የተቀመጠውን የትምህርትና ስልጠና ስታንዳርድ፣ የትምህርትና ስልጠና አገልግሎት አሰጣጥ መስፈርት ማሟላታቸውን፤ አግባብነቱና ጥራቱ ደረጃውን ጠብቆ ስለመፈፀሙ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
  3. አጠቃላይ የትምህርት እና ስልጠና ተቋማት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤ ለሰልጣኞች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና ይሰጣል፤ ብቁ ሆኖ ለተገኘ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤
  4. አጠቃላይ የትምህርት እና ስልጠና ተቋማትን እና የሙያ ብቃትን መረጃ ያደራጃል፤ ያሰራጫል፤ `
  5. የአጠቃላይ የትምህርት እና ስልጠና ተቋማት ብቃት እና ምዘና መከታተያና መገምገሚያ ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ ያደርጋል፤
  6. ፍቃድ ያላቸው የትምህርት እና ስልጠና ተቋማት ጥራታቸው ከስታንዳርድ በታች በሆኑ ተቋማት ላይ የሙያ ብቃት ማረጋገጫውን እስከመሰረዝና እስከ ማሸግ የሚደርስ እርምጃ ይወስዳል፤
  7. በሕገ ወጥ መንገድ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ያገኙ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ላይ የሙያ ፈቃዳቸውን ይሰርዛል፣ ተቋሙንም ያሽጋል፤ አግባብ ባለው የወንጀል ሕግ እንዲጠየቁ ስልጣን ላለው አካል ያሳውቃል፤
  8. የሙያ ብቃት ፍቃድ እያላቸው አግባብ ያለው ህግ በሚጥሱ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
  1. የሙያ ብቃት ፍቃድ ሳያገኙ ወይም በሌሎች ተቋማት የሙያ ብቃት ፈቃድ የሚሰሩ የትምህርት እና ስልጠና ተቋማትን ያሽጋል፤ አግባብ ባለው የወንጀል ሕግ እንዲጠየቁ ሥልጣን ላለው አካል ያሳውቃል፤
  2. ለትምህርት እና ስልጠና ተቋማት ዕውቅና ይሰጣል እውቅና አግኝተው የሚሠሩ ትምህርት ቤቶች በሀገር ደረጃም ሆነ በከተማ ደረጃ በሚወጡ ህጎች የተቀመጡ የትምህርት አግባብነትና ጥራት ደረጃዎችን ማሟላታቸውን ያረጋግጣል፤
  3. በትምህርት ተቋማት የህብረተሰቡን ተሳትፎ ሊያረጋግጡ የሚችሉ አደረጃጀቶች፣ የወላጅ፣ የተማሪ፣ የመምህራን ፎረም፣ የተማሪ ክበባት ስለመኖራቸው ያረጋግጣል፤ እንዲሁም የትምህርት አገልግሎት ክፍያዎች የወላጆችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ እንዲሆን ከተቋማቱ ጋር ይመክራል፤
  4. ከሥራ ዓለምና ከተቋማት የሙያ ብቃት ምዘና ወስደው ብቁ ሆነው ለተገኙ ተመዛኞች የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤
  5. በምዘና ጣቢያነት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ እንዱስትሪዎችን ይለያል፤ ለምዘነና ምቹ ሆነው እንዲደራጁ ያደርጋል፤ የምዘና ስራ ይከታተላል፤ በበላይነት ይመራል፤
  6. ከባለስልጣኑ ውጭ በከተማው አስተዳደር ከሚገኙ ተቋማት ወይም ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የምዘና አገልግሎት መስጠት የሚችሉ አካላትን በመምረጥ ዕውቅና ይሰጣል፤
  7. የሙያ ብቃት ምዘና ማዕከላት፣ የኢንዱስትሪ መዛኞች እና ሱፐርቫይዘሮች አሰራር ለመከታተል የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
  8. ከባለስልጣኑ ባለሙያዎች በመረጃ አያያዝና አደረጃጀት ዙሪያ የሚቀርቡትን የጥናት ኘሮጀክቶች፣ ኘሮፖዛሎችንና ሪፖርቶችን በመገምገም ተግባራዊ ያደርጋል፤
  9. መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ብቃት ያላቸው ሰራተኞች በሚፈለጉበት ወቅት የሙያ ብቃት ምዘና በመስጠት ብቃታቸውን ያረጋግጣል፡፡