ይሁን እንጂ የማዕከሉ አወቃቀርና የደንበኞች አገልግሎት ፍላጎት /Service Need/ ሊጣጣም ባለመቻሉ የከተማችን አስተዳደር ካቢኔ ደንብ ቁጥር 1/2ዐዐዐ ለማሻሻል ባወጣው ደንብ ቁጥር 32/2ዐዐ2 መሠረት ከግንቦት 26 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል በሚል ስያሜ ራሱን ችሎ እንዲዋቀርና ተግባሩም በቦርድ እንዲመራ ሆኖ ተጠሪነቱ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት እንዲሆን ተደርጓል፡፡ የልህቀት ማዕከሉ በአንድ ዋና ዳይሬክተር እና በአንድ ም/ዳይሬክተር በሁለት ዋናና በሰባት ደጋፊ የስራ ሂደቶች በ74 ሰራተኞች በመያዝ ስራዉ እንዲመራ ተደርጓል፡፡የቦርድ አባላቱም ከመሪ መ/ቤቶችና ከኢንዱስትሪዉ እንዲካተቱ ተደርጎ ተዋቁሯል፡፡
እንደገና ተደራሽነትም ለማረጋገጥ የማዕከሉ አደረጃጀት እና አሰራር ለመወሰን ደንብ ቁጥር 64/2007 ዓ.ም በማውጣት የተጠሪነቱ ለዉጥ ሣይደረግ ማዕከሉ ዋና መ/ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ በማዕከል ደረጃ ሆኖ አንድ ዋና ዳይሬክተር እና ሁለት ም/ዳይሬክተሮች የሚመራ በከተማው የተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እንዲኖሩት ተደርጎ ተቋቋመ፡፡ በዚህ መሠረትም ማዕከሉ መዋቀሩን በማስፋት በማዕከል ደረጃ በአንድ ዋና ዳይሬክተር፣ በሁለት ም/ዳይሬተሮች፣ በ3 ዋና የስራ ሂደቶች፣ በ7 ደጋፊ የስራ ሂደቶች እና በ5 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በጠቅላላ ከ330 በላይ ሲቪል ሰራተኞች በመያዝ ተደራሽነቱ በማጠናከር አገልግሎቱን እስከ 20011ዓ.ም መጨረሻ መስጠት ተችሏል፡፡በዚህ አስር ዓመት ጉዞ በ2000 ዓ.ም በ2113 ተመዛኞች የተጀመረዉ እስከ 2011ዓ.ም ብቻ 911,009 ተመዛኝ በመመዘን 479,566 ብቁ ማድረግ ተችሏል፡፡ |
ከሰኔ 2011ዓ.ም ጀምሮ በአዋጅ ቁጥር64/2011 ማዕከሉ እና ሌሎችን ተቋማትን ጨምሮ የትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን በመሆን መዋቅሩን በማስፋት በስምንት ቅርጫፎች፤ በ330 የምዘና ጣቢያዎች፤ 1300 መዛኝ ባለሙያዎች እየታገዘ ለደንበኞች የተጠናከረና የተስፋፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
ከ2000- 2011 ዓ.ም የምዘና ሂደት
ዓመተ ምህረት |
የተመዛኝ ብዛት |
ብቁ የሆኑ ሙያተኞ |
የማለፍ ምጣኔ በ% |
2000 |
2113 |
220 |
10.41 |
2001 |
6589 |
1715 |
26.03 |
2002 |
23185 |
4184 |
18.05 |
2003 |
38309 |
5460 |
14.25 |
2004 |
40661 |
7751 |
19.06 |
2005 |
40636 |
17985 |
44.26 |
2006 |
72235 |
44569 |
61.70 |
2007 |
102553 |
62557 |
61.00 |
2008 |
114291 |
64313 |
56.27 |
2009 |
130259 |
80577 |
61.86 |
2010 |
161192 |
93916 |
58.oo |
2011 |
178,986 |
96319 |
53.77 |
ጠቅላላ ድምር |
911,009 |
479,566 |
52.64 |
ሙያ ብቃት ምዘና ምንድነዉ? |
ሙያ (Occupation):- አንድ ግለሰብ ከማህበራዊ አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ወይም በማምረት በኩል በልምድ ወይም በስልጠና ያገኘዉን ዕምቅ አቅም(Potential) የሚያመለከት ፅንሰ-ሃሳብ ነው፡፡ይሁን እንጂ ግለሰቡ ተግባሩን በተጨባጭ ውጤታማ በሆነ አግባብ ማከናወን መቻል አለመቻሉን የሚያመለክት አይደለም፡፡ ብቃት (Competence):- የሚለው ቃል ደግሞ አንድ ግለሰብ በልምድ ወይም በስልጠና ባገኘው የሙያ መስመር ያለውን እውቀት(Knowledge)፣ የመረዳት ችሎታ(Understanding)፣ ችግርን የመፍታት አቅም (Problem solving capacity፣ ቴክኒካል ክህሎት (Tecnical Skill)፣ አመለካከት (Attitude) እና ስነምግባር (Ethics) ያሳያል፡፡እነዚህ ስድስቱ ችሎታዎች በግለሰብ ዘንድ ዳብረው በቅንጅት መኖራቸውን የሚጠቁም ነው፡፡ ምዘና (Assessment) :- ደግሞ አንድ ግለሰብ ባንድ በተወሰነ የሙያ መስመር የሚፈለገው ዕውቀት፣ ቴክኒካዊ ክህሎት እና አመለካከት አጠቃላይ ብቃት በተቀናጀ አግባብ ያለ መሆኑን ወይም አለመሆኑን ለመዳኘት ሲባል ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጁ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችን( Evidence gathering tools) በመጠቀም መረጃ የመሰብሰብ እና ዳኝነት የመስጠት ሂደትን (Process) የሚያመለክት ጽንሰ-ሃሳብ ነው፡፡
በአጠቃላይ :- የሙያ ብቃት ምዘና በልምድ ወይም በስልጠና የተገኘ የሙያ ባለቤት የሆነን ሰው ብቃት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል መረጃ መሰብሰብና በዚሁ ላይ በመመርኮዝ ዳኝነት የመስጠት ሂደት መሆኑ ቀደም ሲል ተጠቅሷል፡፡በዚህ ሂደት ለመመዘን የቀረበ ያንድ ሙያ መስመር ባለቤት በዚህ መስመር በሚገኝበት ደረጃ የሚጠበቅበትን እውቀት(Knowledge)፣ አመለካከት (Attitude) እና ቴክኒካዊ ክህሎት (Tecnical skill) በተቀናጀ አግባብ አሟልቶ ስለመገኘት አለመገኘቱ የምዘና መሳሪያን (Assessment tools) በመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያነት በመጠቀም ዳኝነት ይሰጠዋል፡፡ገና ብቁ ላልሆነ ተመዛኝም ያለበት የክህሎት ክፍተት በዝርዝር ተነግሮት ክፍተቱን በስልጠና እንዲሞላና ወደ ብቁነት እንዲሸጋገር ምቹ ሁኔታ ይፈጠርለታል፡፡ |