መዛኝ ለመሆን የምልመላ መስፈርት
- የሀገሪቱን ፣ የትምህርትና ስልጠና እና የሙያ ብቃት ምዘናን ፖሊሲ የሚያውቅና ለስርዓቱ ቀና አመለካከት ያለው መሆኑን የሚያረጋገጥ መረጃ ያለው፤
- መዛኝ ለመሆን በፈለገበት ሙያ ቢያንስ 3 ዓመት በኢንዱስትሪው ቀጥተኛ የስራ ልምድ/አገልግሎት/ ያለውና የትምህርት /የስልጠና/ ዝግጅቱ ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- ለስራ ስላለው ተነሳሽነት፣ ስለታማኝነቱ፣ ሀላፊነትን ስለመሸከምና በጽናት ስለመወጣት ብቃቱና ስለሙያዊ ስነምግባሩ ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ወይም ከሌላ ህጋዊ ሰውነት ካለው ተቋም ለትምህርትና ስልጠና ጥራትና ሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርብ
- ለማህበረሰብ ልማት ስላደረገው ተሳትፎና ስላስገኘው ተጨባጭ ውጤት ህጋዊ ሰውነት ካለው አካል ትክክለኛ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ በተለይ በፖርትፎሊዮ ለሚመለመሉ መዛኞች፡፡
- ከሌሎች ጋር በትብብርና በቅንጅት የመስራትና ችግርን የመፍታት ልምድን ያጎለበተ ስለመሆኑ በህጋዊ አካል የተመሰከረለት፣
- በተራ ቁጥር 5 እንዳለ ሆኖ እጥረት ባለባቸው ሙያዎች ግን መዛኝ ለመሆን በፈለገበት ሙያ ቢያንስ 3 ዓመት በኢንዱስትሪው ቀጥተኛ የስራ ልምድ /አገልግሎት/ ያለውና የትምህርት /የስልጠና/ ዝግጅቱ አግባብ ያለው መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- መዛኝ ለመሆን በፈለገበት ሙያ ምዘና ወስዶ ብቃቱን ያረጋገጠና በየደረጃው ከሚመዝነው አንድ ደረጃ ከፍ ያለና በከፍተኛ ደረጃ ደግሞ በተመሳሳዩ ደረጃ የተመዘነ ወይም ለመመዘን ሙሉ ፈቃደኛ የሆነ፣
- በባለስልጣኑ የሚሰጠው የምዘና ሥነ-ዘዴ ስልጠና በብቃት ያጠነቀቀና ሁለት ጊዜ የተግባር የምዘና ልምምድ (Loading) ያደረገ
- ቀደም ሲል በሙስና ወንጀል ምክንያት ተከስሶ ያልተፈረደበት፣ የሥነ-ምግባር ችግር የሌለበት እና መልካም የሙያ ሥነ-ምግባር ያለው
- ደረጃ 5ን የሚመዝን ካልሆነ በቀር ምዘና ከሚሰጥበት የሙያ ደረጃ ቢያንስ በአንድ ደረጃ ከፍ ብሎ የተመዘነ
- ከባለስልጣኑ ጋር የፈረመውን የምዘና ሥምምነት ሰነድ በየሁለት አመቱ ለማሳደስ ፍቃደኛ የሆነ
- ከዚህ በላይ ያለውን መስፈርት የምታሟሉ ባለሙያዎች አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራትና ሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን ቢሮ ቁጥር 603 የምዘና ዝግጅትና አገልግሎት አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት በግንባር ቀርቦ መመዘገብ ይቻለል፡፡