የለሚኩራ ቅ/ጽ/ቤት የሙያ ብቃት ምዘና ስራ በይፋ በዛሬው ዕለት መጀመሩ ተገለፀ፡፡

pic1 1
  pic4 1

29/2/2016
የለሚኩራ ቅ/ጽ/ቤት የሙያ ብቃት ምዘና ስራ በይፋ በዛሬው ዕለት መጀመሩ ተገለፀ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በአዲሱ የለሚኩራ 9ኛው ቅርንጫፍ የሙያ ብቃት ምዘና ስራ በቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ እና የምዘና ዘርፍ ሃላፊ በአቶ ጋትዌች ቱት አማካኝነት በይፋ በዛሬው ዕለት መጀመሩ ተገለፀ፡፡

picc2 1


አዲሱ የለሚኩራ 9ኛው ቅርንጫፍ የሙያ ብቃት ምዘና ስራ በቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት በኮሌጁ ተገኝተው በይፋ ስራ ያስጀመሩት አቶ ጋትዌች ቱት እንደተናገሩት የምዘናውን ስራ ተደራሽነትን ለማስፋት በታቀደው መሰረት በ3ቱ ዘርፎች ማለትም በጤና፣በማዕድን እና በሆቴልና ቱሪዝም መስኮች ምዘና የሚሰጥ ሲሆን በዛሬው ዕለት በምግብ ዝግጅት በአጫጭር ስልጠና አጠናቃቂዎች የብቃት አሀድ ምዘና በይፋ መጀመሩን አብስረዋል፡፡
መንግስት በብልጽግና ጉዞው ትልቁ ትኩረት ከሰጠው አንዱ የአገሪቱን ዜጎች የስራ አጥን ችግር ለመቅረፍ በሚደረገው ከፍተኛ ጥረትና እርብርብ እንዲሁም ስራ አጥነትን ለመቀነስ ለማድረስ እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ ውስጥ የሰለጠነ፣የተመዘነና የበቃ ባለሙያ በገበያው ላይ እንዲፈጠር በከተማችን ከሚገኙ ከማሰልጠኛ ተቋማት እና ከስራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራዞች ቢሮ ጋር በትስስር እና በቅንጅት ተቋማችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ በዛሬው እለት ለአዲሱ ቅ/ጽ/ቤት ስራ መጀመሩ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም እንደገለጹት ዜጎቻችን ሰልጥነው፣ተምረውና በሙያ ብቃት ምዘና አልፈውና በቅተው ስራ ካጡ ድሃ ይሆናሉ፡፡ስለሆነም ድህነትን ለመቅረፍ በትስስር እና በመቀናጀት ከሚመለከታቸው ሴክተር መ/ቤቶች ጋር በመስራት የሙያ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች ወደ ስራ ማስገባትና ተጠቃሚ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል፡፡
እንዲሁም የቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን አቶ መክብብ ተፈራ እንደገለፁት በዛሬው ዕለት የአጫጭር ጊዜ ስልጠና ተመዛኞች ከመነሻው ተመዛኞች የመጡት ከስራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራዝ ቢሮ ሲሆን ኮሌጁ በዋናነት የአጫጭር ጊዜና መደበኛ ሰልጣኞችን ማሰልጠን፣ማብቃትና ማስመዘን እና ባለሙያ ሆነው ከኮሌጁ እንዲወጡ የሚጠበቅ ሲሆን በግል እና በቡድን ተደራጅተው ስራ ፈጥረው ራሳቸውንና አገራቸውን እንዲያገለግሉ እና እንዲጠቀሙ ታሳቢ ይደረጋል ብለዋል፡፡