በአ/አ/ከ/አስ/የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን እና ትምህርት ቢሮ በጋራ በመሆን በ2016 የትምህርት አጀማመር ክትትልና ቁጥጥር ግኝትና የ2015 ዓ.ም የኢንስፔክሽን ግኝት አስመልክቶ ከግል ት/ቤት ባለሃብቶች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

news24 1 news22 1

27/2/2016

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን እና ትምህርት ቢሮ በጋራ በመሆን በ2016 የትምህርት አጀማመር ክትትልና ቁጥጥር ግኝትና የ2015 ዓ.ም የኢንስፔክሽን ግኝት አስመልክቶ ከግል ት/ቤት ባለሃብቶች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ በመርሃ-ግብሩ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት የአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ ትግበራ ተጀምሮ ወደስራ ተገብቷል፤ በዚህ ትግበራ ወቅት ምን ጠንካራ እና ምን ደካማ ጎን አለ የሚለውን በመለየት የተጣለብንን ተልዕኮ ለማሳካትና ከግባችን ለመድረስ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር መነጋገር ተገቢ ነው በመሆኑም የሁላችሁም ሚና ያስፈልጋል፡፡ ዛሬ እዚህ የተገኘነው ባለድርሻ አካላት ደግሞ ወሳኝ ሚና አለን ፤በመሆኑም ተቋማት በግብአት በውጤትና በሂደት እየተፈተሹ እውቅና ይሰጣቸዋል እውቅና ሲሰጣቸው ደረጃቸው በየጊዜው እየተለካ ወደሚፈለገው ደረጃ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡በዚህም ደረጃቸው እየተስተካከለ ይሄዳል ፍተሻም ይካሄዳል በማይስተካከሉት ላይም እርምት ይወሰዳል ብለዋል፡፡

news21 1


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እንደተናገሩት እየተገበርነው ያለው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ሲተገበር ትምህርት እንዴት መጀመር አለበት አጀማመሩ ሂደቱና አፈጻጸሙ ምን ይመስላል የሚለው ታይቷል ፡፡ ትምህርት ዜጋ የሚገነባበት በመሆኑ ከሃብት ሁሉ ሃብት በላይ ትምህርት በመሆኑ በህግና በስርዓት መከናወን አለበት፡፡ አገርን ሊረከብ የሚችል በህግና በስርዓት የሚመራ ዜጋ ይህችን አገር ሊረከብ የሚችል ዜጋ ያስፈልጋል ስለዚህ በተገኙ ግኝቶች ላይ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ያስፈልጋል ፡፡የትውልድ ግንባታ ስራችን በተሳካ መልኩ መከናወን አለበት ብለዋል፡፡
በመድረኩ የ2016 የትምህርት አጀማመር ክትትልና ቁጥጥር ግኝት ሰነድ እና የ2015 ዓ.ም የኢንስፔክሽን ግኝት ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ማጠቃለያ ላይ በስታንዳርድ ኢንስፔክሽን የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የትምህርት ተቋማት የምስክር ወረቀትና ዋንጫ ተበርክቶላቸዋል፡፡

news23 1