የ2015 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የኢንስፔክሽን ትግበራ ውጤት ትንተና ሪፖርት በባለስልጣኑና በት/ቢሮ የጋራ መድረክ ውይይት መደረጉ ተገለፀ፡፡

news38 1
news31 1

news36 1  

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ከከተማው ትምህርት ቢሮ ጋር በመቀናጀት በቂርቆስ ክፍለከተማ መሰብሰቢያ አዳርሽ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የኢንስፔክሽን ትግበራ ውጤት ትንተና ሪፖርት በከተማችን የሚገኙ የመንግስት ት/ቤቶች የትምህርት አመራሮች፣ ር/መ/ምህራን እና ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት መደረጉ ተጠቆመ፡፡ በተጨማሪም የ2016 ዓ.ም የዝግጅት ምዕራፍ በሁለቱ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር መሰረት ከነሃሴ 24-26/2015 ዓ.ም የተሰራ የት/ቤቶች የሱፐርቪዥን ሪፖርት እና በያዝነው በጀት አመት ለመንግስት ት/ቤቶች ለሚጀመረው የእውቅና ፈቃድ ምዘና ባለስልጣኑ ባዘጋጀው የግንዛቤ መፍጠሪያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በመድረኩም የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ እንደገለፁት በየጊዜው የትምህርትን ብቃትንና ጥራትን መፈተሸ እንዲሚያስፈልግ የተናገሩ ሲሆን የትምህርት ስራ ሁልጊዜ አዳጊና ፈታኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡አዲስ አበባ ከተማን የሚመጥን የትምህርት ስርዓትና ጥራት ሊኖረን እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡በከተማችን የሚገኝ አንድ የትምህርት ተቋም ለማስተማር እውቅና ፈቃድ ሊኖረው እንደሚገባ ያስረዱ ሲሆን ዋና ስራ አስኪያጁ በተቀመጠለት ስታንዳርድ መሰረት ሁሉም የመንግስት የት/ርት ተቋማት በያዝነው በጀት አመት በግብአትና በአደረጃጀት ተመዝነው ብቃታቸው ተረጋግጦ ፈቃድ እዲኖራቸው ይደረጋል ብለዋል፡፡ ስለሆነም የመንግስት የት/ቤት ተቋማት ለማስተማር ያሉበትን ቁመና ለማረጋገጥ በምዘና እውቅና ይሰጣቸዋል፡፡በተጨማሪም የመምህራን የሙያ ብቃት በየጊዜው እየተፈተሸ መሄድ እንዳለበት አስረድተዋል፡፡

news34 1



የባለስልጣኑን የ2015 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የኢንስፔክሽን ትግበራ ውጤት ትንተና ሪፖርት ያቀረቡት አቶ አንዋር ሙላቱ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር ሲሆኑ በሪፖርታቸው እንደገለፁት በአጠቃላይ እስካሁን የኢንስፔክሽን አፈፃፀም በከተማው ውስጥ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል 1965(93.9%) ትምህርት ቤቶች የኢንስፔክሽን አገልግሎት ያገኙ መሆኑንና የደረጃ አፈፃፀማቸውም 7(0.4%) ደረጃ 1፣ 1225(62.3%) ደረጃ 2፣ 729(37.1%) ደረጃ 3 እና 3 (0.2%) ደረጃ 4 መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡የደረጃ አፈፃፀሙን በየትምህርት እርከኑ ሲታይ ቅድመ አንደኛ 302 (29.3%) አንደኛ ደረጃ 337 (45.1%) እና 92 (47.1%) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስታንዳርዱን ማሟላት መቻላቸውን ( ደረጃ 3 ) መሆናቸውንና ንጽጽሩም ሲታይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አፈፃፀም የተሻለ መሆኑን ዳይሬክተሩ በመድረኩ ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም በባለስልጣኑ የእቅድ ዝግጅት፣በጀት ግምገማና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ነብዩ ዳዊት አማካኝነት በከተማችን በመንግስት ት/ቤቶች ለሚጀመረው የእውቅና ፈቃድ ምዘና ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠሪያ ሰነድ ለውይይት ተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በያዝነው በጀት አመት በመንግስት ት/ቤቶች የእውቅና ፈቃድ ምዘና የሚጀመር በመሆኑ ባለስልጣኑ በመድረኩ ግንዛቤ መፈጠሩን ለመረዳት ተችሏል፡፡

news37


በመጨረሻም ሁሉም ሰነድ ከቀረበ በኋላ ከተሳታፊዎች ለቀረበው ጥያቄና አስተያየት ምላሽ የተሰጠ ሲሆን አቶ አድማሱ ደቻሳ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ በሰጡት አስተያየት እንደገለፁት ደግሞ በአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ እና ዜጎች የተሻለ ሆነው እንዲቀረፁ ከፍተኛ ስራ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡እንዲሁም የባለስልጣኑ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የኢንስፔክሽን ትግበራ ውጤት ትንተና ሪፖርት የሚያመለክተው አንዳንድ የትምህርት ተቋማት ከደረጃ ሶስት ወደ ደረጃ ሁለት የተመለሱ ት/ቤቶች እንዳሉ ም/ስራ አስኪያጁ ጨምረው አስረድተዋል፡፡በመጨረሻም በ2015 ዓ.ም በውጭ ኢንስፔክሽን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 3 የትምህርት ተቋማት የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

news32 1