ሁሉም ባለድርሻ አካል ማህበራዊ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ተጠቆመ።

3

1/3/2016
ሁሉም ባለድርሻ አካል ማህበራዊ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ተጠቆመ።
በዛሬው ዕለት ፓሽን አካዳሚ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ የሚገኙ ሁለት የችግረኛ ዜጎች ቤቶችን ከ800 ሺ ብር በላይ በማውጣትና በማደስ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የስራ ኃላፊዎች እና የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አመራሮች በተገኙበት ርክክብ ተደረገ።

1 2 4


የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ በመርሐ-ግብሩ ላይ ባስተላለፍት መልዕክት እንደገለጹት ሁሉም ባለድርሻ አካል ማህበራዊ ሃላፊነቶችን መወጣቱ በተለይ ትውልድ ግንባታ ላይ መረባረብና ዜጎችን የተሻለ ደረጃ ላይ ማድርስ ተገቢ እንደሆነና መልካም ስራን ማከናወን የሁላችንም ድርሻ እንደሆነ ያስገነዘቡ ሲሆን ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው መሰራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡ በዚህም መልካም ስራ በማድረግ ቤቶቹን ላደሰው ተቋም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

5 6