መምህር በትምህርት ስራ ውስጥ የማይተካ አካል መሆኑ ተገለጸ፡፡

PIC 3 PIC 5

6/3/2016
መምህር በትምህርት ስራ ውስጥ የማይተካ አካል መሆኑ ተገለጸ፡፡
የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በመምህራን በትምህርት ቤት አመራሮች ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ አተገባባር ላይ የተደረገውን የጥናት ውጤት ለትምህርት ባለድርሻ አካላት አቀረበ፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ እንደገለጹት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚያከናውነው ተግባር አንዱ ጥናትና ምርምር ማካሄድ ነው፡፡ በጥናትና ምርምር ያልተደገፈ ስራ ውጤታማ ነው ተብሎ አይታመንም፤ በመሆኑም ባለስልጣኑ ከተሰጡት ተልዕኮዎች አንዱ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ የትምህርት ጥራትን የማገዝ የመደገፍ ስራ ያከናውናል፡፡
እንደ ባለስልጣን በጥናትና ምርምር ቡድን በባለስልጠኑ እና በውጭ ምሁራን ጥናቶችን ያከናውናል ፡፡ይኧውም የዛሬው ጥናት እንዲጠና ሲታሰብ በኢንስፔክሽን ክትትል ሲደረግ ክፍተት እንዳለው የተለየ ሲሆን ለውሳኔ ለመድረስ ግን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በጥናት መደገፍ አለበት ፡፡
በመሆኑም ተከታታይ የመምህራን የሙያ ማሻሻያ እየተተገበረ ቢሆንም ችግር እንዳለው ጥናቱ የሚያሳይ ሲሆን የዛሬውንም የጥናት ግኝት ግብረ-መልስ ለትምህርት ቢሮ የሚሠጥ ሆኖ ባሉት ጉድለቶች ላይ በጋራ በመስራት የመፍትሄ አካል እንሆናለን ብለዋል፡፡
ዋና ስራ አስኪያጁ የመምህራንን ሙያ ማሻሻያ ለትምህርት ያለውን ፋይዳ ሲያስቀምጡ መምህር በትምህርት ስራ ውስጥ የማይተካ አካል ነው፡፡ የተማሪዎቹ ውጤታማነት እንዲያድግ የመምህሩ የማስተማር ብቃት ጥራት ወሳኝ ነው፡፡መምህራን ወደስራው ሲገቡ እውቀትና የማስተማር ስነ-ዘዴ ሊኖራቸው ይገባል፡፡በዚህም መምህራን ራሳቸውን በየጊዜው እየፈተሹና እየለኩ መሄድ አለባቸው፡፡

PIC 1


ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ መርሃ-ግብር ሲዘረጋ መምህራን ክፍተቶቻቸውን እያዩ እርስ በርስ እየተነጋገሩ ሞያቸውን እያጎለበቱና ከዕለት ወደ ዕለት ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት እንዲሰጡ ነው፤ ስለዚህ ይህ የዛሬው የጥናት ግኝት የመምህራንን አቅም የበለጠ እንዲያጎለብት መምህራንም ሙያቸውን በየጊዜው እንዲያሳደጉ ከፍተኛ ውጤት ይኖረዋል ብለን እንገምታለን፡፡ ከዚህም ሌላ የትምህርት ስራ የመምህሩ ብቻ ሳይሆን ከቤት ጀምሮ የማህበረሰቡ ጭምር በመሆኑ ለተማሪዎች ውጤት ማደግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ጥናቱን ያቀረቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ካሳ ሚካኤል ሲሆኑ እሳቸውም እንደገለጹት የትምህርት ስራ እንዲሻሻል አደዲስ የሆኑ ነገሮችን እንድንሰራ መምህራኖቻችንን ማሻሻል የትምህርት ግብአቶችን የትምህርት አመራሮችን ማሻሻል ሁለንተናዊ የሆነ ለውጥ በተማሪዎቻችን ላይ ማምጣት የሚስችል ተግባር ማከናወን ይጠበቅብናል፡፡

PIC 2


እንደአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፓኬጅ ስድስቱ መርሃ-ግብሮች ተሟልተው ሲገኙ ነው ውጤት የሚያስገኘው ከነዚህ አንዱ የትምህርት የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር ስርኣት ማሻሻያ ሲሆን ይሕ ደግሞ መምህራኖቻችን ሁሌም በተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ራሳቸውን እንዲያበለጽጉ እና እንዲያበቁ ይረዳቸዋል፤
በመሆኑም ባለስልጣኑ የተሰጠውን ሃላፊነት በትምህርት ጥራት ላይ ክትትል እያደረገ ግብረ- መልስ የሚሰጥ ሲሆን ት/ቢሮ ደግሞ በሱፐርቫይዘሮቹ ክትትልና ድጋፍ እያደረገ እንዲበቁ ማድረግ ነው በመሆኑም የዛሬው የጥናት ግኝት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች እና መፍትሄዎቹ ምንድናቸው በማለት የምንለይበት ሲሆን አማራጮቻችንና እድሎቻችንን የምናሰፋበት ነው በመሆኑ፤ የዚህ ጥናት ውጤት ለፖሊሲ አውጪዎች ለት/ሚኒስቴር፣ ለት/ቢሮም የፖሊሲ ግብኣት የሚሆን ውጤት ነው ብለዋል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ላይ የት/ቢሮ አመራሮች፣ ሱፐርቫይዘሮች፣የመንግስትና የግል ት/ቤት ርዕሠ መምህራን፣የክፍለ ከተማና የወረዳ ት/ጽ/ቤት ሃላፊዎች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የትምህርት አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

PIC 4 PIC 6