አለም ያላትን ሃብት ለመጠቀም ብቁ ዜጎችን ማፍራት አስፈላጊ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

14 16 13 17

14/3/2016
አለም ያላትን ሃብት ለመጠቀም ብቁ ዜጎችን ማፍራት አስፈላጊ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በቴ/ሙያ ዘርፍ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ የተደረገ የጥናት ግኝት ለባለድርሻ አካላት ቀረበ፡፡
አቶ ዳኛው ገብሩ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ በመርሃ-ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ከሆነ በቴክኒክና ሙያ የሚሰጠው ስልጠና ለሀገር ግንባታ መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ ሀገር የምትፈልጋቸውን አብዛኛውን በመካከለኛ ደረጃ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች የሚያፈራው ይህ ተቋም ነው ፤የሀገራችን እድገት እንዲሳካ ካስፈለገ ባለሙያው በአግብቡ ስልጠና ተሰጥቶ ገበያው የሚፈልጋቸው ባለሙያዎች ማፍራትና ሙያተኞችን ማብቃት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም በዘርፉ ያሉትን ጉድለቶች በጥናት በመለየትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ያሉትን ጉድለቶች ለማስወገድና የሠለጠኑ ባለሙያዎች ወደኢንስትሪው በማስገባት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ በመግባባት የተሻለ ስራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ከዚህም ሌላ የዛሬውን የጥናት ግኝት ሠምተን የምናልፈው ሳይሆን ችግሩን ለይተን በቀጣይ የተሻለ ስራ ሰርተን በአለም አቀፍና በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እና አለም ያላትን ሃብት ለመጠቀም ብቁ ዜጎችን ማፍራት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

15

ዛሬ እዚህ የተገኘነው ባለድርሻ አካላትም የቀረበውን የጥናት ግኝት ምንድነው የተሰጡትስ ምክረ-ሃሳቦች ምንድናቸው በሚለው ላይ ትኩረት አድርገን ተወያይተን የጋራ አቋም ይዘን ስራችን የተሻለ እንዲሆን ማድረግ ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመሆኑ ዶ/ር ገነነ አበበ ከኢ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኢ የጥናቱን ግኝት ያቀረቡ ሲሆን ጥናቱ እንደሚያሳየው ከዚህ ቀደም ከተጠኑት ጥናቶች ጋር የሚመሳሰል ውጤት ሲሆን ግኝቱ ገበያ ተኮር ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ስልጠና እንደ አዲስ አበባ የተሻሻለ ነገር እንዳለው የሚሳይ ሆኖ የሙያ ደረጃ፣ የማሰልጠኛ መሳሪያ የመመዘኛ መሳሪያ በአብዛኛው የገበያውን ፍላጎት ሙሉ ለሙሉ የሚያንጸባርቁ እንዳልሆኑ ያሳያል፡፡ የትብብርን ስልጠና አስመልክቶ ኢንደስትሪዎች ትልልቅ ማሽኖችን የሚፈልጉ ሙያዎች ላይ ሰልጣኙ ማሽኑ ላይ ጉዳት ይደርሳል በማለት ሰልጣኞች በሌላ ስራ ላይ እንደሚያሰማሩ ያሳያል ፡፡ በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካላት እነዚህንና ሌሎች ችግሮችንም በጋራ ለመፍትሄው ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተው በቀረበው የጥናት ግኝት ላይ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

12 11