በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ላይ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና ተሠጠ፡፡

photo_2023-12-01_17-06-58 photo_2023-12-01_17-06-59

21/3/2016
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ላይ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና ተሠጠ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አዲሱ ስርዓተ ትምህርትን አስመልክት የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና ተሠጠ፡፡
አቶ ዳኛው ገብሩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ በመርሃ-ግብሩ ላይ እንደገለጹት ይህ ስልጠና መዘጋጀቱ ተቋማችን የትምህርት ጥራትን የማስጠበቅ ስራ ስለሚያከናውን ስርአተ- ትምህርቱ የለበትን ደረጃ በሚገባ ተገንዝቦና አውቆ ወደተግባር የሚተረጉም ባለሙያና አመራር በማስፈለጉ መሆኑን ጠቅሰው ከዚህም ጎን ለጎን ተጠያቂነትን አስፍኖ ከስህተት ለመማር እንዲያስችል መሆኑን ተናግረዋል ፡፡ በተጨማሪም አለም የደረሰችበት ደረጃ ላይ ለመድረስና ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት ትምህርት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት አቶ አድማሱ ደቻሳ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት የትምህርት ጥራትን ስራ በአግባቡ መፈጸም እንድንችል ስልጠናው ማስፈለጉን ገልጸው እንደአገር ለማደግ የትምህርት ስርዓት አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸው ማንኛውም ዜጋ ትምህርትን በሚገባ ማግኘት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
የስልጠናው ሰነድ እንደሚያስረዳው የአዲሱ የት/ት ፍኖተ ካርታ በአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ላይ ሰፊ ጥናት የተጠና ሲሆን የጥናቱ ግኝት አንኳር ጉዳዮች መያዙን ገልጾ፤ይኸውም የአጠቃላይ ትምህርት ህግ ማስፈለጉ፣የአጠቃላይ ትምህርት ፖሊሲ ክለሳና የአጠቃላይ የትምህርት የስርአተ ትምህርት ክለሳ መሆኑ ያመላከተ ነው፡፡
ክለሳው ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ የተከናወነ እና የቅድመ ዝግጅት ስራ ፣የጥናት የፍኖተ ካርታ የፖሊሲ ዝግጅት፣ የሥርዓተ ትምህርት ሪፎርም ስራዎች በየጊዜው እንደተሰሩ የቀረበው ሰነድ ያሳያል፡፡
ከዚህም ሌላ የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ትኩረቶች በብቃት ላይ የተመሰረተ ፣የሃገር በቀል እውቀት ፣የሙያና የቀለም ትምህርትን አዋህዶ መስጠት፣ምርትና ምርታማነት ላይ ያተኮረና በቴከተኖሎጂ የተደገፈ መሆኑን የሚገልጽ ሲሆን፤የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ትግበራ፣የተገኘው ውጤት እንዲሁ በዝርዝር ተቀምጧል፡፡
በዋናናት ከባለድርሻ አካላት የሚጠበቀው አዲሱን የአጠቃላይ ትምህርት ሪፎርም ጠንቅቆ ማወቅ፣የመጽሃፍት ትውውቅ በሚገባ መከታተል፣ ስርአተ ትምህርቱን ከአገር በቀል ትምህርት ጋር ማስተሳሰር እንዲሁም 21ኛው ክ/ዘመን የሚጠይቀውን እውቀትና ክህሎት ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ እንደሆነ ያብራራል፡፡
ስልጠናው በጥያቄና መልስ እንዲሁም ውይይት የዳበረ ሲሆን በስልጠናው ላይ የባላስልጠኑ አመራሮች፣ የቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች፣ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል ፡፡

photo_2023-12-01_17-07-00 photo_2023-12-01_17-07-00 (2)