የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መሠረት ያደረገ የአሠልጣኞች ምዘና መስጠት ጀመረ፡፡

ጥር 27/2016 ዓ.ም

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መሠረት ያደረገ የአሠልጣኞች ምዘና መስጠት ጀመረ፡፡


የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መሠረት ያደረገ የአሠልጣኞች ምዘና በተለያዩ ሙያዎችና የምዘና ጣቢያዎች እየሰጠ መሆኑ ታውቋል፡፡

በተለያዩ የምዘና ጣቢያዎች እየተካሄደ ያለውን ምዘና አስመልክቶ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የምዘና ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጋትዌች ቱት የምዘናውን ሂደት አስመልከቶ እንደገለጹት

ምዘናው የሚካሄደው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የተከለሠበት ሁኔታ በመኖሩ እና የሙያ ብቃት ላይ መመዘን ተገቢ በመሆኑ ምዘናው ለአሠልጣኞች እየተሰጠ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

photo_2024-02-05_09-54-09 photo_2024-02-05_09-54-12

የሙያ ብቃት ፓሊሲ ሲቀየር እና የሙያ ደረጃ ሲከለስ አሰልጣኞች ሁሌም በምዘናው ስርዓት የሚያልፋበት አግባብ ቀድሞም የነበረ አሰራር መኖሩን ጠቅሰው ተመዛኞች በምዘናው ብቁ ካልሆኑ ክፍተታቸውን በስልጠና እያሻሻሉ በድጋሚ ምዘናው እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

እየተካሄደ ያለው የምዘና ሂደትም ጥሩ እንደነበረ እና ለተመዛኞች ቀድሞ ገለፃ በማድረግ ዝግጁ እንዲሆኑ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የባለስልጣኑ የቴ/ሙ/ብ/ዝ/አ/አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ራሔል ማሞ በበኩላቸው እንደገለጹት በቴክኒክና ሙያ ስልጠና የሚሰለጥኑ ሠልጣኞች በአዲሱ የሙያ ደረጃ መሰረት ስልጠና እየተሰጣቸው በመሆኑ በተመሳሳይም የአዲሱን የሙያ ደረጃ መሠረት አድርገው ስልጠና የሚያሰለጥኑ አሠልጣኞች በአዲሱ የሙያ ደረጃ ምን ያህል ብቁ እንደሆኑ ምዘናው እየተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

photo_2024-02-05_09-54-10

ምዘናው ሲካሄድ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የተደረጉ ሲሆን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ያዘጋጀውን የምዘና መሣሪያ መሠረት በማድረግ ብቃት ያላቸውን መዛኞችን በመመዘን ብቁ የሆኑት መዛኞች አሠልጣኞችን እንዲመዝኑ የተደረገበት አግባብ መኖሩን ተናግረዋል፡፡

photo_2024-02-05_10-58-32 photo_2024-02-05_10-58-23

በሁሉም ሙያዎች ላይ ምዘና እንደመኖሩ መጠን ምዘናውም በሁሉም ዘርፍ እየተዘጋጀ በተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ አሳውቀዋል፡፡