በ2016 ዓ.ም የእውቅና ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ለሚሰጣቸው የግል የትምህርት ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ

ጥር 28/2016 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2016 ዓ.ም የእውቅና ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ለሚሰጣቸው የግል የትምህርት ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት የዛሬው መርሃ ግብር አላማ  በተደጋጋሚ የሚፈጸም በየጊዜው ግን አዲስ የሚሆን የእውቅና እድሳትና የአዲስ እውቅና ፈቃድ መስጠት ላይ የሚያተኩር ሲሆን በእቅዳችን 805 የሚሆኑ የግል የትምህርት ተቋማት የእውቅና እድሳት ይደረጋል፡፡በመሆኑም ቅድመ ዝግጅት  በማድረግ እውቀት ጉልበትና ጊዜ በአግባቡ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በመጠቀም ፍተሻውን ማከናወን እድንችል ዝግጅት እንድታደርጉና በዚህም መድረክ ስለ ሂደቱ እንድንወያይና የጋራ ግልጽነት መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ መደረኩ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

photo_2024-02-15_00-43-23 photo_2024-02-15_00-43-16

አቶ አድማሱ ደቻሳ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅና የጥራት ዘርፍ ሃላፊ በመድረኩ እንዳስገነዘቡት የእውቅና ፈቃድ እድሳት ለግል ተቋማት እንደሚሰጥ ገልጸው የግብኣት ማዘጋጀት ደግሞ ለእውቅና ፈቃድ ሳይሆን ለተማሪዎች የተሻለ ትምህርት ለመስጠት እንዲያግዝ መሆኑን ጠቅሰው  በቼክሊስቱ መሰረት  ሁሉም  ተቋማት እንዲዘጋጁ አሳስበዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ሁሉም ተቋም  ህጋዊ ሆኖ እንዲቀጥል እንፈልጋለን፡፡  ህጋዊ ባልሆነ መልኩ ግን አንድም ተቋም እንደማይቀጥል አስገንዝበዋል፡፡ 

photo_2024-02-15_00-42-55

የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነዱን ያቀረቡት አቶ ያሬድ ካሳ የባለስልጣኑ የእውቅና ፈቃድ እድሳት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ ተቋማት በቂ ግብአትና አደረጃጀት መፍጠራቸውን ለማረጋገጥ፣ ከስታንዳርድ ጋር በማነፃፀር ያሉባቸውን ክፍተቶች በመለየት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ፣ለተስተዋሉ ክፍተቶች ግብረ መልስ በመስጠት በቀጣይ መታረማቸውን ለማረጋገጥ፣ የተስተዋሉ ክፍተቶች ላይ ድጋፍና ክትትል ለሚያደርገው ባለድርሻ አካል በማሳወቅ ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትል እንዲያገኙ ለማድረግ፣ከስታንዳርድ በታች የሆኑ ተቋማትን በመለየት የእርምት እርምጃ በመውሰድ ለማህበረሰቡ ለማሳወቅ፣ ዜጎች ጥራቱ በተረጋገጠ የትምህርት ተቋማት የመማር መብታቸውን ለማስጠበቅ እንደሆነ እውቅና ፈቃድ የሚደረገው ያቀረቡት ሰነድ ያስረዳል፡፡

photo_2024-02-15_00-43-20 photo_2024-02-15_00-43-12

ከዚህም ሌላ በምዘና ወቅት በትምህርት ተቋማት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶች፣ እውቅና ፍቃድ ለማደስ ከትምህርት ተቋማት የሚጠበቁ ግዴታዎችን፣እውቅና የማይታደስባቸው ምክንያቶች፣የትምህርት ተቋማት መብት፣እውቅና ፍቃድ እድሳት የግዜ ገደብ፣ከእውቅና ፍቃድ እድሳት በኋላ የባለስልጣኑ ተግባርና ሀላፊነት፣እድሳት ያገኘ የትምህርት ተቋማት ግዴታን ሰነዱ በዝርዝር አስቀምጧል፡፡
በእለቱ ከቅድመ አንደኛ፣አንደኛና መካከለኛ ደረጃ እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ያሉ 805 ያህል የትምህርት ተቋማት ተገኝተው በቀረበው ሰነድ መሰረት ጥያቄዎች እንዲሁም አስተያየቶች ያነሱ ሲሆን ሰፊ ውይይት እና ለተነሱት ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው የሥራ ሃለፊዎችና አመራሮች ምላሽ ተሰጥቶበታል ፡፡

photo_2024-02-15_00-43-27