ሰራተኛው ራሱን እንዲያበቃና ሙያዊ ስነ-ምግባር በተላበስ መልኩ እንዲያገለግል ወቅቱን የጠበቀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም

በአዲስ አበባ  ከተማ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን  የእውቅና ፍቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት በተከለሰው የእውቅና ፍቃድ እድሳት ቼክሊስት ዙሪያ  የዘጠኙ ቅ/ፅ/ቤት ዳይሬክተሮች፣ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ፡፡

photo_2024-03-03_10-47-15 2

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና  የጥራት  ዘርፍ  ሃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በመርሀ-ግብሩ መክፈቻ  ላይ እንደተናገሩት እንደከተማ በትምህርት ዘርፍ እየተደረገ ያለውን  ትልቅ  ጥረትና ትኩረት ባለስልጣኑ እንደ ባለስልጣን የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባር  እየተወጣ ይገኛል፤በመሆኑም ለተቋማት አገልግሎት በምንሰጥበት ወቅት በሙያዊ ስነ-ምግባር በተላበሰ መልኩ እና በተከለሰው ቼክሊስት መሰረት ወጥነት ባለው መልኩ በማገልገልና ለህግ ያልተገዙትን  ተጠያቂ በማድረግ  የበኩላችንን  ሀላፊነት ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

photo_2024-03-03_10-47-27

የባለስልጣኑ የእውቅና ፍቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ካሳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የባለሙያ ግዴታዎች፣እርምጃ የሚያስወስዱ ተግባራት፣ የተቋማት መብት፡ተግባርና ኃላፊነት የታዩ ጥንካሬና ክፍተቶች  በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን ከየካቲት1 እስከ ግንቦት 30 ቅድመ አንደኛ 465 አንደኛና መካከለኛ 279 ሁለተኛ ደረጃ 64 በድምሩ 808  ተቋማት  በተቀመጠው ጊዜ ገደብ መሰረት እውቅና ፍቃድና እድሳት የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡

photo_2024-03-03_10-47-32

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ በመርሃ-ግብሩ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት  ፈጣንና  ፍትሀዊ  አገልግሎት በመስጠት ብልሹ አሰራርን በጋራ  በመከላከል   ተቋማቱን  በስታንዳርድና ቼክሊስት በመመዘን ዜጎች ጥራቱ በተረጋገጠ  ትምህርት ተቋማት የመማር መብት ልናስጠብቅ ይገባል ብለዋል፡፡