የትምህርት ጥራትና ተገቢነትን ለማረጋገጥ የባለድርሻ አካላት ሚና ሰፊ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የ2016 ዓ.ም የስራ ዘመን በጀመሪያዎቹ 6ወራት የተከናወኑ ተግባራትን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ኢትዮጵያ ካላት በጀት ከፍተኛውን የመደበቸው ለትምህርት ዘርፍ እንደመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለትምህርቱ ዘርፍ ሃላፊነት አለበት፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንደ ባለስልጣን ያሉበትን ሀላፊነቶች በአግባቡ እየተወጣ ይገኛል፡፡

photo_2024-03-03_11-00-30

በዚህም መሰረት ትምህርት የሀገር ምሰሶ መሆኑን አስበን ሁለገብ ስብዕና ያለው ትውልድ ለመፍጠር የጋራ መግባባት በመፍጠር ያሉብንን ችግሮች በመፍታትና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ ህግን በማስከበር ልጆቻችንን ጥራቱ በተጠበቀ የትምህርት ተቋም  የመማር መብታቸውን ልናስከብር ይገባል ብለዋል፡፡ 


photo_2024-03-03_11-00-15
photo_2024-03-03_11-00-12

የባለስልጣኑ እቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ዳዊት የባለስልጣኑን የስድስት ወር ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች አፈፃፀም፣የቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም፣የአበይት ስራዎች አፈፃፀም፣ጠንካራና ደካማ ጎኖች፣ያጋጠሙ ችግሮች የተፈቱበት መንገድና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫን በሪፖርቱ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ ከቤቱ ለተነሱት ጥያቄዎችም ከሚመለከታቸው የሥራ ሃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡

photo_2024-03-03_11-00-07 photo_2024-03-03_11-00-26