በናሙና ኢንስፔክሽን ትግበራ ላይ ለማዕከልና ለቅ/ጽ/ቤት ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡

የካቲት 12/2016 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የትምህርትና ጥራት ማረጋገጥ ምርምር ዳይሬክቶሬት በናሙና ትግበራ ኢንስፔክሽን ላይ ለማዕከልና ለ9ኙም ቅ/ጽ/ቤት የአጠቃላይ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡የባለስልጣኑ የአጠቃላይ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥ ባለሙያ አቶ ያሬድ አበራ በዋናነት በትምህርት ዘርፍ ልማት ፕሮግራም የጥራት ማረጋገጥ፣የኢንስፔክሽን ፍይዳ፣የናሙና ኢንስፔክሽን እና የኢንስፔክሽን መሪ መርሆች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰተዋል፡፡

photo_2024-03-03_11-08-49 photo_2024-03-03_11-08-45 photo_2024-03-03_11-08-41

የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አንዋር ሙላት እንደገለፁት በከተማ ደረጃ ስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ከህዳር ጀምሮ እስከ ጥር ድረስ ለቅድመ አንደኛ ደረጃ  ት/ቤቶች መሰጠቱን ጠቁመው  በዚህም መሰረት የኢንስፔክሽን ያፈጻጸሙን ሂደት፣ዉጤታማነት ለመፈተሽ  እና በመመሪያው መሰረት  መተግበሩን ለማየት ናሙና ኢንፔክሽን እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ናሙና የሚሰራው ከማዕከል ትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት እና ከቅ/ጽ/ቤት ባለሙያዎች ጋር በጋራ በመሆን ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ናሙና እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡