ብቁ እና ተወዳዳሪ ትውልድ ለመፍጠር ብቃት ያለው አስልጣኝ መኖሩ የግድና አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ፡

የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በሙያ ብቃት ምዘና ዘርፍ በአዲሱ ምዘና አጀማመር ዙሪያ ለግል ኮሌጅ ባለቤቶችና ዲኖች ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ መርሀ-ግብሩ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ልጆቻችን መሰልጠን ያለባቸው ብቁና ተወዳዳሪ በሆነ አሰልጣኝ እንደመሆኑ የትኛውም አሰልጣኝ በምዘና ስርዓት በማለፍና ክፍተቶችን በአጫጭር ስልጠናዎች በመሙላት ስራውን በብቃት በመወጣት ትውልድን ሊያበቃ ይገባል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ብልሹ አሰራርን በጋራ በመታገልና በማጥፋት ተወዳዳሪ ዜጋ እንፍጠር የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

photo_2024-03-03_11-15-31 photo_2024-03-03_11-15-35

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የምዘና ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጋትዌች ቱት ማንኛውም አሰልጣኝ በምዘና ስርዓት በማለፍ እና ክፍተቶች ካሉበትም  የታዩበትን ክፍቶች በስልጠና በመሙላትና ምዘናውን እንዲያከናውን እናንተም ከእኛ ጋር በመሆንና ያለንን ትልቅ  የጊዜ  ሀብት  ተጠቅመን በጋራ በመስራት ተግባራቶቻችንን ልንፈጽም ይገባል ብለዋል፡፡

photo_2024-03-03_11-15-27 photo_2024-03-03_11-15-23

የባለስልጣኑ የቴ/ሙያ ብቃት ምዘና አገልግሎት ዝግጅት አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ራሄል ማሞ የውይይት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ምርትና ምርታማነትን፣ አገልግሎት አሰጣጥን፣ አለማቀፋዊ ተወዳዳሪነትና የበቃ የሰው ሀይል ለኢዱስትሪው ለመመገብ ይህን መሰረት በማድረግ በእውቀት የዳበረ በክህሎት የበለፀገ በአስተሳሰብ የተስተካከለ የሰው ሃይል ከመፍጠርና ብቃቱን የሚያረጋግጥበት ስርዓት ተዘርግቶ ሀገራችንን ወደተሻለ ደረጃ ማሻገርና የበቃ የሰው ሀይል ከማፍራት ጋር መነሻ አድርጎ እየተሰራ ያለ ስራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ከተወያዮች ለተነሱት ጥያቄዎችና ማብራሪያን የሚሹ ሃሳቦች ከአመራሮቹ ምላሽ ተሰቶባቸዋል፡፡