ባለስልጣኑ "የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል 6ኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተከናወነ።

c3 c4 c7
c11 c12 c3

 

ሀምሌ 13 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን "የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ"በሚል መሪ ቃል 6ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በዛሬው እለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በለቡ ወረዳ የተካሄደ ሲሆን የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት አገር የምትበለጽገው ተፈጥሮአዊ ሚዛኗ ሲጠበቅና ለዜጎቿ ምቹ የሆነ አካባቢ ስትሆን ነው፡፡

c1 c2


በመሆኑም አገራችንን ምቹ መኖሪያ የምናደርጋት እኛ ዜጎቿ ነን ፡፡ይህን ታሳቢ አድርገን ዛሬ የምናከናውነው ተግባር ሀገርን የማበልጸግ አንዱ አካል በመሆኑ ወደፊት ይህን አጠናክረን እንቀጥላለን፤በቀጣይም ዛሬ የተከልነውን ችግኝ ተንከባክበን የምናሳድገው ሲሆን ዛሬ እዚህ ተገኝተን ችግኝ ስንተክል ለሀገራችን አሻራችንን እያኖርን እንደሆነ መረዳት አለብን ብለዋል፡፡

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃኑ አበራ በመርሃ-ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ይህ ተግባር አገርን የመገንባትና ለትውልድ የማሰብ አጀንዳ በመሆኑ ዜጎች የራሳቸው ተግባር አድርገው በከፍተኛ ጉጉት በየአመቱ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ያከናውናሉ፡፡ በመሆኑም ዛሬ ባለስልጣኑ ይህን ተግባር በክፍለ ከተማው በማከናወኑ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ የበላይ አመራሮች፣የዘጠኙ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆችና በማዕከልና በቅ/ጽ/ቤት ያሉ ሰራተኞች እንዲሁም የትምህርት ተቋማት የተሳተፉ ሲሆን በእለቱ አስርሺህ ችግኝ ተተክሏል፡፡