ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራን ለማስጀመር ከትምህርት ተቋማት ጋር የቤት እድሳት ርክክብ አደረገ፡፡
(ሀምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራን ለማስጀመር በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ ወረዳ 9 ለሚገኙ 19 የአቅመ ደካማ ወገኖች ቤት የማደስ ስራ ለማከናወን ርክክብ አድርጓል፡፡
በዚህም የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚታደሱት ቤቶች በባለስልጣኑ ዋናው መስሪያ ቤት እና በዘጠኙ የባለስልጣኑ ቅ/ፅ/ቤቶች እንዲሁም በከተማችን የሚገኙ የግል የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባባር የሚሰሩ ሲሆን የቤት እድሳት ስራው በቅርብ ቀን የሚጀመር እና በቅርቡ ተሰርቶና ተጠናቆ ባለቤቶቹ የሚረከቡ እንደሆነ ታውቋል፡፡