ትምህርት ቤቶቹ የተማሪዎችን ምዝገባ ቀጥሎ የተቀመጡትን ነጥቦች አስተካክለው እንዲመዘግቡ ተፈቀደ፡፡
1.ክብርት ከንቲባ ያስቀመጧቸውን የስራ መመሪያ እና አቅጣጫዎችን እንዲሁም የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የአሰራር አቅጣጫዎችን ህግና ስርአት በሚያዘው ብቻ ያለመሸራረፍ አሟልተው የመተግበር ግዴታ ያለባቸው መሆኑ፤
2.የትምህርት ፖሊሲ፣ስርዓተ ትምህርት፣መመሪያዎችና አሰራሮችን ሙሉ ለሙሉ አሟልተውና አክብረው መተግበር እንዳለባቸው፤
3.ለ2017 የትምህርት ዘመን እውቅና ፍቃድ እድሳት በሌላቸው(4) ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን መዝግበው እንዲቀጥሉ፤
4.እውቅና ፍቃድ እድሳት ያላቸው (12) የቅድመ አንደኛ ፣አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከ28/10/2016 ዓ.ም ጀምረው የእውቅና ፍቃድ እድሳት እንዲያደርጉ መግባባት ላይ መደረሱ፤
5.የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሆነው በእውቅና ፍቃድ እድሳት ተመዝነው መስፈርቱን ያላሟሉ (2) ት/ቤቶች ልክ እንደሌሎች ት/ቤቶች በማስጠንቀቂያ ቀጥለው እስከ ህዳር 30/2017 ዓ.ም ድረስ ስታንዳርዱን አሟልተው እንዲመዘኑ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት ማረግ ያለባቸው መሆኑ፤
6. የትምህርት አገልግሎት ክፍያ እና የመመዝገቢያ ክፍያ ለሌሎች የትምህርት ተቋማት በወረደው አሰራር መሰረት በባንክ ስርአት ብቻ መጠቀም ያለባቸው መሆኑ፤
7.የተማሪዎች መማሪያ መፅሀፍት ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በመቀበል አሰራሩ በሚያዘው መሰረት ብቻ ለተማሪዎች ተደራሽ የማድረግና ከዚህ ውጭ ሌሎች መፅሃፍቶችን በሀርድም ሆነ በሶፍት ኮፒ ለተማሪዎች ማድረስ የማይችሉ መሆኑ፤
8.ት/ቤቶቹ ክትትል ቁጥጥርና ድጋፍ ለሚያደርጉ አካላት በራቸውን ክፍት የማድረግና የመተባበር ግዴታቸውን እንዲወጡ እንዲሁም በትምህርት ጥራት ዙሪያ የሚሠጣቸውን ግብረ-መልሶች ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ ያለባቸው መሆኑ፤
ይህን አስተካክለው ተማሪዎችን እንዲመዘግቡና ቀጣይ የት/ት ፖሊሲ፣ስርዓተ ት/ት ፣መመሪያና ደንቦችን በሙሉ የትግበራ ሂደቱን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በጥብቅ እንደሚደግፍ፣እንደሚከታተልና እንደሚቆጣጠር በማሳሰብ የተማሪዎች ምዝገባ ተፈቅዶላቸዋል፡፡