(ሀምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም) የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት መሪ አቅድ እና የዝግጅት ምዕራፍ እቅድን የጋራ የማድረግና የማናበብ ተግባር ተከናወነ፡፡
አቶ አድማሱ ደቻሳ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ የመድረኩን አላማ እንደገለጹት ለሁሉም የበጀት አመቱ ማስጀመሪያ እንደሆነ ገልጸው ፤በዋናው ቢሮ እና በቅ/ጽ/ቤት በሁሉም ዘርፍ ያለው ባለሙያ እቅዱን ተረድቶት በቂ መግባባት ላይ መድረስ እንደሚያስችል ገልጸው ፈጻሚው ጋር በአግባቡ የደረሰ እቅድ ውጤታማ የሆነ ተግባርን ማከናወን ያስችላል ብለዋል፡፡
አቶ ጋትዌች ቱት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት በ2016 በጀት አመት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው የ2017 በጀት አመት የመነሻ እቅድ እንደዚህ በጋራ መድርክ መቅረቡ የጋራ የሆነ ግንዛቤና አቋም ኖሮን ስራችንን የጋራ ማድረግ ያስችለናል ብለዋል፡፡
አቶ ነብዩ ዳዊት የእቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክትር የመነሻ እቅዱን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን አስተያየትና ግብዓት ተሰብስቦበታል ውይይትም ተደርጎበታል፡፡
በመድረኩ ላይ የባለስልጣኑ አመራሮች፣የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች፣ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡