የባለስልጣኑ የውጭ ጥናት ግምገማ ተካሄደ፡፡

r2 r3 r1

 

(ሀምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በውጭ አጥኚ ምሁራን ያስጠናውን "Factors affecting the achievements of grade 12 students in national exams in Addis Ababa" በሚል እርሰ-ጉዳይ የባለስልጥኑ አመራሮች፣የቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች እንዲሁም የባለስልጣኑ የትምህርት ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች  በተገኙበት ግምገማ ተካሄደ፡፡

 የባለስልጣኑ ምክትል ስራስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንደተናገሩት የከተማችን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አፈፃጸም ምን ይመስላል፣የብሄራዊ ፈተና ዋናዋና የውጤት ችግሮችስ ምንድን ሊሆኑ ይችላሉ በማለት በውጭ አቅም በጥናት ለመለየት ለሃገር እና ለከተማችን ለትምህርት ስርዓቱ ጥራት ውጤታማነት የሚያግዝ ጥናት እየተጠና መሆኑን አስረድተዋል፡፡

 በግምገማውም በአጥኚው ቡድን አማካኝነት ጥናቱ ለአመራሮች ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን በጥናቱ የተገኙ ክፍተቶች የትግበራ ስትራቴጂ ተነድፎ በቀጣይ ቀናት ተስተካክሎ እንዲቀርብ ከአጥኚው ቡድን ጋር የጋራ ስምምነት መደረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡