ባለስልጣኑ ባደረገው ድንገተኛ ኢንስፔክሽን 44 ኮሌጆች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

 (ሀምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት በ2016 ዓ.ም ለ59 ኮሌጆች በተከናወነ ድንገተኛ ኢንስፔክሽን የተገኙ ግኝቶችን መሰረት በማድረግ

1.ከፍተኛ የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ ጥሰት እና የስትራቴጂ ጥሰት የታየባቸው 18 ኮሌጆች የታገዱ ሲሆን እነርሱም

  1. ብራይት ኮሌጅ ልደታ ካምፓስ
  2. ብራይት ኮሌጅ ጀሞ ካምፓስ
  3. ሸገር ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
  4. ልቀት ኮሌጅ አራት ኪሎ ካምፓስ
  5. ልቀት ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
  6. ላየን ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
  7. ሀርመኒ ኮሌጅ ቂሊንጦ ካምፓስ
  8. አልፋ ኮሌጅ ላንቻ ካምፓስ
  9. አፍሪካ ቤዛ ኮሌጅ
  10. አረና መልቲ ሚዲያ ኮሌጅ
  11. ጌጅ ኮሌጅ ሾላ ካምፓስ
  12. ሳትኮም ኮሌጅ
  13. ኩዊንስ ኮሌጅ አምስት ኪሎ ካምፓስ
  14. ሀርመኒ ኮሌጅ ሀና ማርያም ካምፓስ
  15. ኩዊንስ ኮሌጅ መድሀኒዓለም ካምፓስ
  16. ሀጌ ኮሌጅ
  17. ኪያሜድ ኮሌጅ እንቁላል ፋብሪካ ካምፓስ
  18. ኩዊንስ ኮሌጅ ዩሀንስ ካምፓስ

2.የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ ጥሰት የታየባቸው 18 ኮሌጆች የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው

  1. ግሬት ቡልቡላ ኮሌጅ
  2. ቢኤስቲ ኮሌጅ
  3. ክቡር ኮሌጅ
  4. ፋርማ ኮሌጅ
  5. ቅድስት ልደታ ኮሌጅ
  6. ኤግል ኮሌጅ
  7. አፍሪካ ጤና ኮሌጅ
  8. ናሽናል ኮሌጅ
  9. ሀርቫርድ ኮሌጅ
  10. ሰቨን ስታር ኮሌጅ
  11. ራዳ ኮሌጅ
  12. ሬፍትቫሊይ ኮሌጅ ካራሎ ካምፓስ
  13. ኬቢ ኮሌጅ
  14. ያጨ ኮሌጅ
  15. ኪያሜድ ኮሌጅ 22 ካምፓስ
  16. ናይል ሳይድ ኮሌጅ
  17. ኪያሜድ ኮሌጅ አየርጤና ካምፓስ
  18. ዊልነስ ኮሌጅ

  3. መለስተኛ የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ ጥሰት የታየባቸው 8 ኮሌጆች የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው

  1. ያኔት ኮሌጅ 6 ኪሎ ካምፓስ
  2. ዳማት ኮሌጅ ጊወርጊስ ካምፓስ
  3. ያኔት ኮሌጅ ሰፈረ ሰላም ካምፓስ
  4. ኤክስፕረስ ኮሌጅ
  5. ቅድስት ሃና ኮሌጅ
  6. ግራንድ ማርክ ኮሌጅ
  7. ኩዊንስ ኮሌጅ ሃና ማሪያም ካምፓስ
  8. ሀራምቤ ኮሌጅ ሜክሲኮ ካምፓስ

በዚህም አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ባለስልጣኑ ያሳወቀ ሲሆን ፤ ተቋማቱ እንደደረሳቸው አስተዳደራዊ እርምጃ መሰረት በአስር ቀናት ውስጥ እርምትና ማስተካከያ በማድረግ በጽሁፍና በአካል ሪፖርት በማድረግ ለባለስልጣኑ የማያሳውቁ ከሆነ እንደየደረጃው ቀጣይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳውቋል፡፡