የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስተባባሪነት በክፍለ ከተማው የክረምት የበጎ ፈቃድ የሚታደሱ የአቅመ ደካማ ቤቶች የማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተካሄደ፡፡

(ሀምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም) በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስተባባሪነት በክፍለ ከተማው ወረዳ 9 አስተዳደር በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚገነቡ 19 ቤቶችን የማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተካሂዷል፡፡

H7 H6 H10

 አዲስ አበባ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብርሃም ታደሰ በማስጀመሪያ መርሀ-ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በጎነት ወሰን የሌለው የአይምሮ ትልቅ እርካታ የሚያስገኝ እንደሆነ ጠቁመው በትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ አካላት በበጎ ፍቃድ ተግባራት ላይ በመሳተፍ አርአያነት ያለው ተግባር ሰርተዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

 በዘንድሮ የክረምት መርሀ-ግብርም በከተማ ደረጃ 3500 አቅም የሌላቸው ዜጎች የቤት እድሳት እንደሚደረግና ከነዚህም ውስጥ ባለ 8 ወለል የቤት ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል ያሉ ሲሆን ባለፉት 5 ዓመታት በከተማ ደረጃ 27 ሺ በላይ የአቅመ ደካማ ቤቶች መገንባቱን ጠቁመዋል፡፡

 የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ከለውጡ ወዲህ በርካታ ሰው ተኮር ተግባራት ላይ ትኩረት በማድረግ ሰውን ማዕከል ያደረገ የቤት እድሳት ተግባራት ተከናውነዋል ሲሉ የገለጹ ሲሆን የዛሬውን ቤቶች አስተባብረው ለሚያሰሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን  እና በትምህርት ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሃብቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከመደበኛ ተግባራት ጎን ለጎን በበርካታ ሰው ተኮር ተግባራት ተሳታፊ እንደሆነና አቅም የሌላቸውን ወገኖች ለመደገፍ ለሚሰሩት ስራ በትምህርት ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት ምስጋና በማቅረብ ቤቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለተጠቃሚዎች ማስረከብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

H2 H1 H3

 በመርሀ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብርሃም ታደሰ፣የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው፣በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ፣የባለስልጣኑ የጥራት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ፣የባለስልጣኑ የምዘና ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጋትዌች ቱት፣የ9ኙ ቅ/ጽ/ቤቶች ስራ አስኪያጆች፣ የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን፣በ11ዱም ክፍለ ከተማ በትምህርት ዘርፍ የተሠማሩ ባለሃብቶች እንዲሁም የወረዳ 09 ምክር ቤት አባላት፣የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

H8 H9 H7
H4 H11 H12

ምንጭ፡-ኮልፌ ኮሙኒኬሽን