(ነሀሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የትምህርት ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳሬክቶሬት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሚስተዋለውን በባለሙያዎች መካከል ያለውን የእውቀትና የክህሎት ክፍተት ለመሙላት ያለመ ስልጠና ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ አቶ አንዋር ሙላት የባለስልጣኑ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ገልፀዋል፡፡
የስልጠናው ዋና አላማ አቶ አንዋር ሲገልጹ በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ሶስቱም አካላት ከማዕከል እስከ ቅ/ጽ/ቤት የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኢንስፔክሽን ባለሙያዎች፣የእውቅና ፈቃድና እድሳት እና በከተማችን የ11ዱ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ባለሙያዎች የጋራ አረዳድና በባለሞያዎች መካከል ያለውን የእውቀት እና የምዘና ክህሎት ለማቀራረብ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ስለሆነም ስልጠናውን ከፌዴራል ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እና ከሚኒስቴሩ በተጋበዙ ሁለት የዘርፉ ባለሙያዎች በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ፣በቴክኒክና ስልጠና ስትራቴጂ፣በቴ/ሙ/የውስጥ ምዘና መመሪያ፣በስርዓተ ስልጠና እና በቴ/ሙ/ኢንስፔክሽን ሙያ በ2016 በጀት አመት አፈፃፀም ሂደት ላይ የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት እና አፈጻጸምን መነሻ በማድረግ የባለሙያዎችን ክፍተት በመለየት ክፍተቶችን በሚያጠብ መልኩ ስልጠናው ርዕሰ-ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑን አቶ አንዋር ሙላት ገልፀዋል፡፡