ሁሉም አካል ሌብነት እና ብልሹ አሠራርን በኔነት መንፈስ ሊታገል እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

(ነሀሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም)የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሳምራዊት ጌታቸው ከባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ባሰለፍነው በጀት ዓመት በማዕከል እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን እንደነበረ ገልፀዋል::

photo_2024-10-01_01-36-11

ሙስና የጋራ ጠላት መሆኑን ሁሉም አካል በልቡ አስርፆ ችግሩን ለመቅረፍ መረባረብ ያለበት ሲሆን ለዚህም የፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ለባለስልጣኑ ሠራተኞች እና ለባለድርሻ አካላት ስልጠናዎችን በመስጠት ሰፊ የግንዛቤ መስጫ መድረኮች በማዘጋጀት ለውጦች እንዲመጡ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በሌላም በኩል ብልሹ አሠራሮችን በተመለከተ የሚመጡ ቅሬታዎችን እና ጥቆማዎችን በመለየት በመተንተን ከሚመለከተው አካል ጋር በተገቢው በደብዳቤ ተደራሽ እንዲሆን የተደረገበት አግባብ ሲኖር ችግሩም እንዲፈታ አስፈላጊው ክትትል የማድረግ ስራዎች በመስራት ተጠያቂ መሆን ያለበት አካል በሕግ እንዲጠየቅ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የሀብት ምዝገባ በተመለከተ ከማዕከል እስከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ላሉ ስራ አስኪያጆች ዳይሬክቶሬቶች እና ቡድን መሪዎች የሀብት ምዝገባ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

የሙስና ተጋላጭነት መሠረት በማድረግ የአሠራር ስርዓት ጥናት የተሰራበት አግባብ ሲኖር የቀረበውን ምክረ ሃሳብ ለሚመለከተው አካል ተደራሽ የማድረግ ስራ በመስራት የማወያየት ምክረ ሃሳቦች ምን ላይ ደረሱ የሚለውን ለውጡን በመገምገም የክትትል ድጋፍ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት ካሉ የፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ጋር በጋር በመሆን በመናበብ ስራዎች በመሰራታቸው በ2016 በጀት አመት በከተማ ደረጃ ካሉ ተቋማት ውስጥ ዳይሬክቶሬቱ የተሻለ አፈፃፀም በማምጣት እንዲሁም የሙስና ተጋላጭነት የጥናት ግኝት በተሰጠ ምክረ ሃሳብ የተቋሙን የአሰራር ስርዓት በማሻሻል ረገድ የተሻለ ስራ በመሰራቱ የምስክር ወረቀት የዋንጫ እና የፕሪንተር ሽልማት የተበረከተላቸው መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

አገራችንን በተገቢው ለማሳደግ እና ለውጥ ማምጣት የምንችለው ሌብነት እና ብልሹ አሰራሮችን መዋጋት ስንችል ስለሆነ በየደረጃው ያለው አመራር እና ባለሙያ የሚሰጠውን የስራ ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

photo_2024-10-01_01-36-16 photo_2024-10-01_01-36-11