ባለስልጣኑ በዛሬው ዕለት የማዕድ ማጋራት አደረገ፡፡

በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች ጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም የነገ ቀን በጋራ አክብረዋል፡፡በዕለቱም በባለስልጣኑ ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋዮች እና በጡረታ ከባለስልጣኑ ለተገለሉ ሰራተኞች የማዕድ ማጋራት ተካሂዷል::

photo_2024-10-09_05-58-23 photo_2024-10-09_05-58-10 photo_2024-10-09_05-58-00


ዕለቱን አስመልክቶ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ ባስተላለፉት መልዕክት በመስጠታችን እናተርፍበታለን በመስጠታችን እንጠቀማለን ከሰጠነው በላይ ይጨመርልናል ያሉ ሲሆን እንኳን ለ2017 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳቹህ አደረስን አዲሱ ዓመት የሰላም የፍቅር የአብሮነት ይሁንልን በማለት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

photo_2024-10-09_05-58-04 photo_2024-10-09_05-58-13

ጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም የነገ ቀን
የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፋት!!