ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የጉለሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅሩ ገቢሳ እንደገለፁት መምህራን እና የት/ቤት አመራሮች ሙያቸውን እንዲያሳድጉ የሙያ ፍቃድ ምዘና መካሄድ ከተጀመረ በርካታ አመታትን ማስቆጠሩን አስታውሰዋል፡፡በዚህም በ2016 ዓ.ም በጀት አመት ላይ የመምህራን እና ርዕሰ መምህራን የሙያ ፍቃድ ምዘና የተሰጠ ሲሆን የምዘና ውጤታቸውን መሰረት በማድረግ የማህደረ ተግባር ምዘና ለማካሄድ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም የፁሑፍ ምዘናውን ላለፍ መምህራን እና ርዕሰ መምህራን ማዕደር ክዋኔ ምዘና ከመካሄዱ በፊት ለተመዛኞችና ለመዛኞች ስልጠና እና ገለጻ እንደሚደረግ አሳውቀዋል፡፡
ምዘናው የተሳካ እንዲሆንም የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን የፁሑፍ ምዘናቸውን በአግባቡ እንዲደርሳቸው በማድረግ እና በምዘናው ወቅት ምዘናው በተገቢው ሁኔታ እንዲካሄድ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል፡፡
በዕለቱ የጉለሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የመምህራን ሙያ ፍቃድ አሰጣጥና እድሳት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ አሸናፊ መለሰ በ2016 ዓ/ም የተካሄደውን የመጀመሪያ ደረጃ መምህራንና የት/ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት የጽሁፍ ምዘና ሂደት በምን መልኩ እንደተካሄደ የሚያመላክት ሰነድ አቅርበዋል፡፡