ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የጉለሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ላይ የማህደር ተግባር ምዘናዎች እያካሄደ መሆኑን የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሸን ባለሙያዎች ተመልከተናል፡፡
በዚህም በፀሐይ ጮራ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ላይ በተገኘንበት ወቅት ምዘናውን ሲያስተባብሩ ያገኘናቸው የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሱፕርቫይዘር የሆኑት አቶ ጌታቸው ታረቀኝ ምዘውን አስመልክቶ እንደገለፁት በምዘናው ላይ የተመደቡት ተመዛኝ መምህራን አብዛኛዎቹ ተገኝተው የማህደር ተግባር ምዘናውን እያከናወኑ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ምዘናው መምህሩ ራሱን የተሻለ ሆኖ እንዲወጣ እና ራሱን እንዲያበቃ እንዲሁም በራስ መተማመን የሚጨምርለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
![]() |
![]() |
አቶ ጌታቸው አክለውም የመምህራን እና የርዕሰ መምህራን ምዘና መልካም የመማር ማስተማር ሂደት የሚፈጥር እና በተማሪዎች ውጤት እና ጥሩ ስነምግባር እንዲኖር ለማስቻል የሚረዳ በመሆኑ በትምህርት ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ራሳቸውን በንባብ በማብቃት በየአመቱ በሚሰጡ ምዘናዎች ላይ በመሳተፍ የሙያ ፍቃድ ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል ፡፡
የማህደር ምዘናውን ለማከናወን በእንጦጦ አምባ ት/ቤት እና በብርሃን ጮራ ት/ቤት የተገኙ እንዳንድ ተመዛኞች በበኩላቸው እንደገለፁት ምዘናው ጥሩ መሆኑን ገልጸው መዛኞችም በጥሩ ስነምግባር የታነፁ በመሆናቸው ያላቸውን መረጃዎች በአግባቡ ለማስመዘን መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡
![]() |
![]() |
በምዘናው ሂደትም መምህራኖች ማንኛውንም ስራቸውን ሲሰሩ በመረጃ እና በማስረጃ በማስደገፍ በአግባቡ መስራት እንደሚገባ ትምህርት ማግኘታቸውን፣እንዲሁም ስራቸውን በተገቢው ጥራት መስራት የሚገባቸው መሆኑን የተገነዘቡበት ምዘና ሲሆን ተማሪዎች አስፈላጊውን እውቀት ይዘው ወደ ሚፈልገው የትምህርት ደረጃ እንዲሸጋገሩ የመምህራን ብቃት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የእውቅና ፍቃድ እና እድሳት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ አስቴር አበበ ሂደቱን አስመልክቶ እንደገለጹት በፁሑፍ ፈተና 62.5 እና ከዛ በላይ ያመጡትን መምህራንና ርዕሰ መምህራንን በ12 በተመረጡ የትምህርት ተቋማት ላይ በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት በሁለት ሽፍት በጠዋት እና በማታ በመክፈል በዛ መሰረት እየተስተናገዱ ይገኛሉ፡፡ምዘናው በፕሮግራሙ መሰረት ነገ የሚጠናቀቅ ቢሆንም በተለያየ ምክንያት መመዘን ያልቻሉትን የሚቀጥለው ሳምንት እንደሚመዘኑ ተናግረዋል፡፡
በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ 622 ተመዛኝ መምህራን እና ርዕሰ መምህራን የማህደር ተግባር ምዘናን የሚወስዱ ሲኖሩ አብዛኛዎቹም ትላንት ጀምረው በተመደቡበት ተቋም ላይ በመገኘት ምዘናውን እያከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የማህደር ተግባር ምዘና በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ስር ባሉ ዘጠኙም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችም እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፤