የመምህራንና የትምህርት አመራሮች የማህደረ ተግባር ምዘና ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የእውቅና ፈቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት ባለፈው በጀት አመት የጹሑፍ ምዘና ወስደው መስፈርቱን ላሟሉ የማህደረ ተግባር ምዘና እየሰጠ መሆኑን ተገልጿል፡፡


በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የእውቅና ፈቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሮማን በለው በበጀት አመቱ ከተያዘው ተግባር አንዱ የጽሑፍ ምዘናውን ላለፉ መ/ራንና የትምህርት አመራሮች የማህደረ ተግባር ምዘና ማካሄድ መሆኑን ገልጸው ይህን ማሳካት እንዲያስችል ምዘናውን ለሚወስዱ መ/ራንና የትምህርት አመራሮች የምዘና ማናበቢያ አስመልክቶ ኦረንቴሽን በመስጠት፣ምዘናውን የሚያካሂዱ መ/ራንና የት/ቤት አመራሮችን በመለየት እንዴት መመዘን እንደሚገባቸው ኦረንቴሽን መሰጠቱን አንስተዋል፡፡የምዘና ጣቢያን ከማመቻቸት አኳያ ለትምህርት ተቋማት አማካይ የሆኑ 4 የምዘና ጣቢያዎችን በመምረጥ የጣቢያዎቹ ምቹነትን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የማረጋገጥ ስራ መሰራቱን አንስተዋል፡፡

photo_2024-11-18_03-29-01 photo_2024-11-18_03-29-07

አያይዘውም በ2016ዓ.ም የጹሑፍ ምዘና ከወሰዱ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች መካከል የጹሑፍ ምዘና የማለፊያ ነጥብ ያስመዘገቡ 672 መ/ራንና አመራሮች የማህደረ ተግባር ምዘና እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑንና በዚህም በመጀመሪያው ዙር እንዲወስዱ ከሚጠበቀው 501 ተመዛኞች ውስጥ ባሳለፍነው አርብና ቅዳሜ በተደረገው ምዘና 405 መ/ራንና 9 የት/ቤት አመራሮች በድምሩ 414 የማህደረ ተግባር ምዘናውን ማጠናቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡

ዳይሬክተሯ አክለውም ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተሰጠው አቅጣጫ በቀጣይም የፊታችን አርብና ቅዳሜ ለ2ኛ ደረጃ መ/ራንና የትምህርት አመራሮች ምዘናውን በመስጠት የማጠቃለል ስራ ለመስራት መዘጋጀታቸውን ለዚህም ተገቢው ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

photo_2024-11-18_03-29-04 photo_2024-11-18_03-29-10

የማህደረ ተግባር ምዘናውን አጠቃላይ ሂደት በተመለከተ አስተያየት ከሰጡ ተመዛኝ መ/ራን መካከል የእንግሊዘኛ ቋንቋ መ/ር የሆኑት መ/ር ገብረጨርቆስ ክንፈ የማህደረ ተግባር ምዘና ሂደቱ እጅግ በጣም ግልጽነት የተሞላበትና የተቀመጠውን ማናበቢያ ተከትሎ መረጃና ማስረጃን በተገቢው በማሳየት የተካሄደ እንደሆነና ሂደቱ ከጠበቁት በላይ እንደሆነባቸውና በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ሀሳባቸውን ሲቀጥሉም ብቁ ለሆኑ መ/ራንና የትምህርት አመራሮች በወቅቱ የብቃት ማረጋገጫ ባለፉት ጊዜያት የሚሰጥበት ሁኔታ አለመኖሩ ቅሬታን ይፈጥር ስለነበረ በዘንድሮው አመት ይህ ሊታረም ይገባል ብለዋል፡፡
ምንጭ፡- ለሚ ኩራ ቅ/ጽ/ቤት