ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የኮልፌ ቀራንዮ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ላይ የማህደር ተግባር ምዘናዎች አካሄደ፡፡
የማህደረ ተግባር ምዘናውን ለመመዘን በጀነራል ዋቆ ጉቱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያገኘናቸው መምህርት ወይንሸት እንደተናገሩት የፈተናው ሂደት ጥሩ መሆኑን እና የተደሰቱበት መሆኑን በመግለፅ አቅማቸውን የሚፈትሽና ያላቸውን እውቀት የሚያዳብር መሆኑን ነግረውናል፡፡
እንዲሁም የማህደረ ተግባር መዛኝ አቶ አንግዳ ሳህለ እስካሁን በመዘንኩበት ሂደት ጥሩ የሚባል የፋይል አያያዝ እና አደረጃጀት አይቻለው ይህ ተግባር የሚበረታታ ነው ያሉ ሲሆን በዚህም መምህራን ለትምህርት ዘርፉ ትኩረት የሰጡ መሆኑን ተረድቻለው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የኮልፌ ቀራንዮ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የእውቅና ፍቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ካሳ መኩሪያ እንደገለፁት ፈተና ከመጀመራቸው አሰቀድመው ለመዛኞችም ለተመዛኞችም ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እንዲሁም ስነምግባር በተላበሰ መልኩ እንዲጠናቀቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የጋራ መግባባት የተፈጠረበት ሁኔታ መኖሩን ገልጸው በምዘና ሂደቱ ላይ ተግዳሮቶች የነበሩ ቢሆንም ከማዕከል ጋር በጋራ በመስራት የተሳካ የምዘና ሂደት መከናወኑን ገልፀውልናል፡፡
እየተሰጠ ያለውን የማህደረ ተግባር ምዘና ሂደቱን የማእከል የእውቅና ፍቃድና እድሳት እና የኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች በቦታው በመገኘት ምልከታ አድርገዋል፡፡