ባለስልጣኑ የ19 አቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በማሳደስ ርክክብ አደረገ፡፡

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በከተማው ውስጥ ያሉ የግል የትምህርትና ስልጠና ተቋማትን በማስተባበር በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ለሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖች 19 ቤቶችን በማደስ ርክክብ አከናወነ፡፡

photo_2024-11-18_03-39-29 photo_2024-11-18_03-39-26

አቶ ዳኛው ገብሩ የትህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ በመርሃ-ግብሩ ላይ እንደተናገሩት በከተማችን ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ የልማት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ይህን ሰው ተኮር የልማት እንቅስቃሴ ከተሰጠን ተልዕኮ በተጨማሪ በየጊዜው በበጎ አድራጎትና በቤት ግንባታ የምንሳተፍ ሲሆን በዚህም ዓመት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ 19 ቤቶችን በከተማችን ያሉትን የግል የትምህርትና ስልጠና ተቋማት በማስተባበር 10 ሚሊየን ብር በሆነ ወጪ በማሰራት ርክክብ አከናውነናል፡፡በግንባታው የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ባለቤቶች ስራ አስኪያጆች የባለስልጣኑም አመራሮች ርብርብ በማድረግ ስራውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ አድርገዋል ብለዋል፡፡

ከዚህም በላይ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ባለቤቶች በኮሚቴው ውሰጥ በመሳተፍ ከፍተኛ የሆነ ሚናቸውን ተወጥተዋል፤በዚህም ሊመሰገኑ ይገባል ያሉ ሲሆን እኛም መደበኛ ስራችንን እየሰራን ልማትንና ማህበራዊ ግዴታችንን መወጣት ስላለብን ወደፊትም እንዲህ ያለውን የልማት ስራ አጠናክረን እንሰራልን በማለት በስራ ላይ የተሳተፉትንም ባለሃብቶች አመስግነዋል፡፡

photo_2024-11-18_03-39-36 photo_2024-11-18_03-39-33

አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ በመርሃ-ግብሩ ላይ እንደተናገሩት መንግስት አቅመ ደካሞችን በመርዳት የዜጎችን ህይወት በማሻሻል ከፍተኛ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣንም በክፍለ ከተማው ለሶስተኛ ጊዜ እንደዚህ አይነት ወገኖችን የመደገፍ ተግባር እየሰራ በመሆኑና ባለስልጣኑ ትውልድንም የሚገነባ ስለሆነ እንደዚህ አይነት ቤቶችን ሰርታችሁ ስታስረክቡ በነዚህ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች ደስ ብሏቸው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማድረግ አገርና ትውልድን መገንባት በመሆኑ በዚህ ስራ ላይ በመሳተፋችሁ ትልቅ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል፡፡

photo_2024-11-18_03-39-38 photo_2024-11-18_03-39-43

የቤት ግንባታው የተሰራላቸው ወገኖችም በተደረገላቸው መልካም ነገር አመስግነው ይህ የተደረገልን ነገር አዲስ እንደመወለድ እንቆጥረዋለን፤ሁላችሁንም እናመሰግናለን የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም በዚህ ተግባር ላይ ለተሳተፉና ስራውን ላስተባበሩ አካላት ሁሉ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡