በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የክትትልና ቁጥጥር፣የእውቅና ፍቃድ እድሳት፣የድንገተኛ ኢንስፔክሽን እና የሙያ ብቃት ምዘና ግኝት ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት ቀረበ፡፡

ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ፤በስራና ክህሎት ቢሮ የተደረገ የክትትልና ቁጥጥር ሪፖርት፣የእውቅና ፍቃድ እድሳት፣የድንገተኛ ኢንስፔክሽን ግኝት እና የሙያ ብቃት ምዘና ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት ቀረበ፡፡

ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ በመልዕክታቸው እንደገለጹት የበቃ ክህሎት ያለው ዜጋን ለመፍጠር በቂ ስልጠና ለመስጠትና በዘርፉ የሚታዩ ክፍተቶችን በማስተካከልና ጠንካራ ጎኑን አጠናክሮ ለመሄድ እንደሃገር፣እንደከተማ እንደ ተቋም የተያዘውን አላማና ግብ ማሳካት እንድንችል በጋራ ርብርብ ማድረግና ተቀናጅተን ይበልጥ ውጤታማ መሆን ይጠበቅብናል በማለት መልዕክታቸውን አስተልፈዋል፡፡

photo_2024-12-09_23-57-22 photo_2024-12-09_23-57-39

አቶ ጋትዌች ቱት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ እንደተናገሩት እየሰራን ያለነው ለአንድ አላማ ነው ስለዚህ ችግሮቻችንን በመነጋገር አንድ አቅጣጫ መያዝ ያስፈልጋል፤በመሆኑም በጋራ በመስራት ከተማችንን ከፍ እናድርጋት ብለዋል፡፡

አቶ አምባቸው ግርማይ በስራና ክህሎት ቢሮ የተቋማት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደገለጹት በተለያየ አደረጃጀት ያለን ለአንድ አላማ የቆምን ስራችንና ውጤታችን ለአንድ አላማ በመሆኑ ችግሮችን በጋራ በመረባረብ መፍታት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

photo_2024-12-09_23-57-30 photo_2024-12-09_23-57-39

የባለስልጣኑ የእውቅና ፍቃድ እና እድሳት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ካሳ የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የ2017 ዓ.ም የእውቅና ፈቃድ እድሳት፣የድንገተኛ ኢንስፔክሽንና የምዘና አፈፃፀም ውጤትና የግኝት ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ሪፖርቱ ከማሰልጠኛ ኮሌጆችና ተቋማት አንፃር፣ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር፣የ2017 ዓ.ም የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የእውቅና ፈቃድ እድሳት ውጤት ትንተና፣በ2017 ዓ.ም ኮሌጆች በስታንዳርዶች ያስመዘገቡት ውጤት፣በድገተኛ ኢንስፔክሽን በቼክሊስቱ መሰረት የታየ ግኝት፣ምዘናን አስመልክቶ የትብብር ስልጠና፣የምዘና ሂደት እና ሌሎችንም ጉዳዮች ሪፖርቱ ላይ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

photo_2024-12-09_23-57-32 photo_2024-12-09_23-57-36

አቶ ፀጋዬ ግዛው በስራና ክህሎት ቢሮ የግል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን መሪ በቢሮ የተደረገ የክትትልና ቁጥጥር ሪፖርት አቅርበዋል፡፡በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ የተለያዩ ሃሳቦች አስተያየቶችና ጥያቄዎች ከቤቱ የቀረቡ ሲሆን ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡

በመርሃ-ግብሩ ማጠቃለያ ላይ በእውቅና ፍቃድ እደሳት ምዘና ከተሰራላቸው 71 ኮሌጆች መካከል የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የማሰልጠኛ ተቋማት እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡