ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን"ወጣቶችን ያማከለ የጸረ ሙስና ትግል የነገን ስብዕና ይገነባል"በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ እንዲሁም በአገር አቀፍ ለ 20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የጸረ ሙስና ቀን የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች አክብረዋል፡፡
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ጋትዌች ቱት በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልእክት የሰለጠነ ህሊና እና አመለካከት ሲኖረን ሙስናን መከላከል እንችላለን ያሉ ሲሆን እንዲሁም ሁላችንም በምንሰጠው አገልግሎት ውስጥ ስለ ሙስናና ብልሹ አሰራር በቂ ግንዛቤ በመያዝ የምንሰጠውን አገልግሎት ከሙስናና ብልሹ አሰራር የጸዳ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
የባስልጣኑ የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ባለሙያ አቶ መስፍን ደገፉ ሀገር አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን በአል ለማክበር የተዘጋጀ መነሻ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በተለይም ወጣቶች ሙስናና ብልሹ አሰራር በከተማዋ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ፖለቲካዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት በመቀነስ ረገድ ድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻልና የጸረ ሙስና ትግሉ ባለቤት እንዲሆኑ ማድረግ ዋና አላማ ነው ብለዋል፡፡
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን, የባለስልጣኑ አማካሪ አቶ ብርሃኑ ተሾመ ወጣቶችን ያማከለ እየበለፀገች ያለችዋን ኢትዮጲያን ለማየት እያንዳንዱ ሰው አስተዋጽኦ በማበርከት የሀገር እድገት ጸር የሆነውን ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን በመታገል ሀገራችን ወደፊት አንድ እርምጃ ማስቀደም አለብን ብለዋል፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይም የጥያቄና መልስ ውድድር የተከናወነ ሲሆን በውድድሩ ለተሳተፉ ሰራተኞችም ሽልማት ተበርክቶላቸው መርሃ ግብሩ ተጠናቋል፡፡