(ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን”ሰብአዊ መብትን ያከበረ የኤች አይቪ አገልግሎት ለሁሉም“በሚል መሪ ቃል 36ኛው የጸረ ኤች አይቪ ቀን የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት በፓናል ውይይት ተከብሯል፡፡
አቶ ስንታሁ ጎሹ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ባለሙያ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በአለም አቀፍ እና በሀገራችን ያለውን የኤች አይቪ አሁናዊ መረጃ፣የተመዘገቡ ዋና ዋና ውጤቶች እና ተግዳሮቶች እንዲሁም የመፍትሄ አቅጣጫዎች የገለጹ ሲሆን የኤች አይቪ የስርጭት ምጣኔ በ2010 ከነበረበት መቀነስ ቢቻልም አሁንም ድረስ መዘናጋቶች እንደሚስተዋሉ ጠቅሰው በቀጣይም ህብረተሰቡ በቀጥታ የሚሳተፍባቸውን የተለያዩ አደረጃጀቶችን መልሶ ማደራጀት፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንዲሁም በ ኤች አይቪ ዙሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ማእከላትን ማጠናከርና ማስፋፋት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ ባሰተላለፉት መልዕክት በኤች አይቪ ኤድስ ምክንያት የሚከሰት የሞት መጠን ቢቀንስም አሁንም ድረስ ቫይረሱ አሳሳቢ ነው ያሉ ሲሆን በተለይ ወጣት እና አምራች ሀይሉን እያጠቃ ይገኛል ስለዚህ ሁላችንም የቫይረሱን አሳሳቢነት በመረዳት እና ግንዛቤያችንን በማስፋት እራሳችንን ልጠብቅ ይገባል ብለዋል፡፡
አቶ ጋትዌች ቱት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ ኤች አይቪ በወገኖቻችን ላይ ከባድ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል መጠንቀቅ የገባዋል የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በዕለቱ በቀረበው ሰነድ ላይ ከባለስልጣኑ ሰራተኞች ሃሳብ አስተያየት የተሰጠ ሲሆን ውይይትም ተደርጎበታል፡፡