በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች ጳጉሜ 4/2016 ዓ.ም የህብር ቀን በጋራ አክብረዋል፡፡ዕለቱን አስመልክቶ አቶ ዳኛው ገብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች ውህድ በመሆኗ ደምቀን በብዙ ባህላችን በአንድነታችን አስተሳሰረን መድመቅ አለብን ያሉ ሲሆን እኛ ኢትዮጵያውያን በቅኝ ያልተገዛን በመሆናችን ልንኮራ ይገባል ብለዋል፡፡
በዕለቱ ጳጉሜ 3 የተከበረውን የሉአላዊነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ቀደም ሲል የአገር መከላከያ ሰራዊት በመሆን ያገለገሉና በአሁን ወቅት በባለስልጠኑ በተለያዩ ሙያዎች ላይ እያገለገሉ ያሉ ባለሙዎች ምስጋና እና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡
ጳጉሜ 4/2016 ዓ.ም የህብር ቀን
ኅብረት ለሰላማችን!!