ባለስልጣኑ የአብሮነት የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት በዓል የሆነውን የመስቀል እና የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

(መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት በዓል የሆነውን የመስቀል እና የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ውይይት አድርገዋል፡፡ስለ በዓላቱ ታሪካዊ ትውፊት መነሻ እና አከባበር ሰነድ የባለስልጣኑ አማካሪ በሆኑት አቶ ሰለሞን አለማየሁ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ 

photo_2024-10-09_06-03-59 photo_2024-10-09_06-04-02

አቶ ሰለሞን እንደገለጹት በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚገኙ ሃይማኖታዊም ሆኑ ህዝባዊ በዓላት ትውፊታቸው ተጠብቆ ሃገራችንን በአለም አደባባይ በማስጠራት የሃገራችን ታላቅ ኩራት በመሆናቸው በዓላቱ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ባገናዘበ መልኩ በአብሮነት ስሜት ልናከብራቸው ይገባል ብለዋል፡፡ከዚህ ሌላ በዓላቱ በብዙ ህዝብ በአደባባይ የሚከበሩ በመሆናቸው ያለምንም የጸጥታ ስጋት እንዲያከበሩ ሁሉም አመራር እና ሰራተኛ የሚጠበቅበትን ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ተሳታፊዎችም በበኩላቸው በዓሉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከጸጥታ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ እና የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

photo_2024-10-09_06-04-14 photo_2024-10-09_06-04-08 photo_2024-10-09_06-04-17