ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!" 17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዛሬው ዕለት ተከበረ፡፡

 ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን 17ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ሁሉም የባለስልጣኑ ሰራተኞች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።  

photo_2024-11-13_22-39-21 photo_2024-10-14_05-02-43

አቶ ዳባ ጉተታ የባለስልጣኑ የትምህርት ምዘናና ምርምር ጥናት ባለሙያ ባስተላለፉት መልዕክት ሰንደቅ ዓላማን ስናስብ ሀገራችንን አሰብን ማለት ነው ሀገራችንን እና ባንዲራችንን ሁልጊዜም በልባችን እናስብ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡በመርሃግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ሰራተኞች ብሔራዊ የህዝብ መዝሙር ዘምረዋል፡፡

photo_2024-11-13_22-39-26 photo_2024-11-13_22-39-24 photo_2024-11-13_22-39-32

"ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!"