ባለስልጣኑ የተቀናጀ የትምህርት ምዘና እና ቁጥጥር አስተዳደር ስርዓት (IEARMS) ፕሮጀክት ስራው ያለበትን ሂደት ገመገመ፡፡

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ከአልሚ ድርጅት ጋር የተፈራረመውን የተቀናጀ የትምህርት ምዘና እና ቁጥጥር አስተዳደር ስርዓት (IEARMS) ፕሮጀክት ሶፍት ዌር የማበልፀግ ስምምነት ያለበትን የስራ ሂደት የባለስልጣኑ ከፍተኛ ባለስልጣኖች፣ዳይሬክተሮች፣ቡድን መሪዎች እንዲሁም ባለሙያዎች በተገኙበት ገምግሟል፡፡

photo_2024-11-13_23-06-44 photo_2024-11-13_23-06-47 photo_2024-11-13_23-06-50

ባለስልጣኑ የትምህርትና ስልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ፣በስሩ ያሉትን ችግሮችን ለማሻሻልና የአሰራር ስርዓቱን ለማዘመን የሚያግዘው ሶፍትዌር እንዲበለጽግለት ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሶፍት ዌሩን ለማልማት በጨረታ ከአሸነፈው ጋም ቴክኖለጂስት ኢምፖርተር ካምፓኒ ጋር በመፈራረም ስራውን ጀምሮ የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት የደረሰበትን የስራ ሂደት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገምግሟል፡፡

የባለስልጣኑ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታምራት እንደገለፁት ግምገማው ለድርጅቱ ግብኣት የሚሆን መሆኑን በመግለፅ የባለስልጣኑን ሶስቱን ዋና ስራ ሂደቶችን ማለትም የሙያ ብቃት ምዘናን፣የእውቅና ፈቃድና እድሳት እንዲሁም የአጠቃላይ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ የትምህርትና ስልጠናን አጠቃላይ አሰራር ስርዓቱን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሻሽለውና እንደሚያዘምነው ገልጸዋል፡፡

photo_2024-11-13_23-06-41 photo_2024-11-13_23-06-53

ከአልሚ ድርጅቱ የመጡት ቡድን አባላት ስራው ያለበትን ሂደት ገለጻ ባደረጉበት ወቅት ለተነሡ ጥያቄዎችና ግልጽነትን ለሚሹ ሃሳቦች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡