ባለስልጣኑ በ2017 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃጸም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡

ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃጸም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡
የእቅድ አፈፃፀሙን ያቀረቡት የባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ነብዩ ዳዊት ሲሆኑ በአፈፃፀሙ ላይ እንደተገለጸው በዝግጅት ምዕራፍ ላይ እቅዶችን በማቀድ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ወደ ስራ የተገባ መሆኑን ተናግረዋል፤እንዲሁም የአንደኛ ሩብ አመት የአበይት ተግባራት አፈጻጸም ከ2016 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

photo_2024-11-18_03-22-53 photo_2024-11-18_03-22-58

በዚህም በአጠቃላይ ትምህርት በድንገተኛ ኤንስፔክሽን አፈጻጸም እንዲሁም በእውቅና ፈቃድ እድሳት ተግባራት ላይ ያለው አፈጻጸም መልካም እንደሆነ ሪፖርቱ ያሳያል ከዚህም ሌላ በሙያ ብቃት ምዘና ዘርፍ ጥሩ አፈጻጸም እንዳለ ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡

በሌላ በኩል የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም በማሳደግ ብልሹ አሰራር ውስጥ የሚገቡ ባሙያዎች መቀነስ መቻሉ፣ የአመራር ተከታታይ ድጋፍና ክትትል በማጠናከር በዘርፍና ቅ/ጽ ቤቶች ማሻሻል መቻሉ እንዲሁም የማህበራዊ ሃላፊነት ለመወጣት የማዕድ ማጋራት እና የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት እድሳት በልዩ ትኩረት ውጤታማ ማድረግ መቻሉ በሩብ አመቱ የተገኙ ውጤቶች መሆናቸውን አሳወቀዋል፡፡
ከዚህም ሌላ ዳይሬክተሩ የ2017 የ1ኛ ሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል ግኝት ሪፖርት በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪ አቶ አምላኩ ተበጀ የባለስልጣኑ የአሰራር ጥራት ቁጥጥር ቡድን መሪ የተቋማት ክትትልና ቁጥጥር ግኝት ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

photo_2024-11-18_03-22-55 photo_2024-11-18_03-23-03

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ጋትዌች ቱት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም የነበሩበትን ክፍተቶች ቀስ በቀስ በመቅረፍ አሁን ላይ ጥሩ መሻሻል እንዳለ ተናግረዋል፡፡ ባለሙያውም ተቆጥሮ የተሰጠውን ስራ ሕግና መመሪያን ተከትሎ በአግባቡ መስራት የሚገባው እንደሆነና አገልግሎት አሰጣጣችን ከሌብነት እና ከብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን ጥረት መደረግ አለበት ብለዋል፡፡ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ በመድረኩ ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት አጠቃላይ ስራዎች ያሉበት ደረጃ ጥሩ መሆኑን ገልጸው አፈፃፀማቸውም ካሳለፍነው በጀት አመት አንጻር የተሻለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

photo_2024-11-18_03-22-44 photo_2024-11-18_03-22-58

በቀጣይም የክህሎት ክፍተት ያለባቸው ሰራተኞች እየተለዩ ስልጠና በመስጠት የማብቃት ስራዎች መሰራት ያለበት ሲሆን ሁሉም ሰራተኛ ስራውን በጥሩ ስነምግባር መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፤ እንዲሁም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተረጋጋ ተቋም እንዲሆን እና መልካም አስተዳደር ለማስፈን ሕግና ስርዓትን በተከተለ አግባብ ስራዎች መከናወን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በዕለቱ ከቅ/ጽ/ቤቶችና ከማዕከል የተመረጡ ዳይሬክቶሬቶች ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡ከዚህም ሌላ በቀረቡት ሰነዶች ላይ አስተያየት የተሠጠ እና ውይይት የተደረገ ሲሆን በመድረኩም ላይ ከሴክተር መስሪያ ቤት የተጋበዙ ባለድርሻ አካላት እና በማዕከል እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያሉ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች በውይይቱ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡