በአዲሱ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ስልጠና እና የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የእውቅና ፍቃድ እድሳት ዳይሬክቶሬት በአዲሱ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ስልጠና እና የትምህርት ስልጠና ፖሊሲ ዙሪያ ከስራ እና ክህሎት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ በመክፍቻ ንግግራቸው የስልጠናውን አስፈላጊነት እንደገለጹት በስራ ላይ ክፍተት የሚፈጥሩ ጉዳዮችን ተናቦና ተቀናጅቶ ለተገልጋይ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ስልጠናው እንደሚረዳ ገልጸው ሁሉም በጋራ ስራውን እና ተግባሩን አውቆ ሲመራ ውጤታማ የሆነ ስራ መስራት ይቻላል ብለዋል ፡፡

photo_2024-12-23_00-28-21 photo_2024-12-23_00-28-23

ስልጠናውን የሰጡት ከስራና ክህሎት ቢሮ የመጡት የስርዓተ ስልጠና እና የማሰልጠኛ መሳሪዎች ዴስክ ሀላፊ ትዕግስት ከበደ ከውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ጋር በተያያዘ እንዲሁም ያሉት ሙያዎች ምን ይመስላሉ እና ያላቸውን ይዘት፣የቆይታ ጊዜ እንዲሁም የስርአተ ትምህርት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ስልጠና የሰጡ ሲሆን ፤አቶ አሉላ መዝገበ በስራ መረጃ አያያዝ ዙሪያ በውጭ ሃገር ሰራተኛ ስምሪት የዜጎችን ደህንነት እና ጥቅም ለማስጠበቅ ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እንዲሁም ስራና ሰራተኛን የተመለከተ አገልግሎት የሚሰጡበት እና የሚያጋጥማቸውን መሰረታዊ ችግሮች የሚፈቱበት የአሰራር ስርዓት እንደሆነ በሰጡት ስልጠና ላይ ገልጸዋል፡፡

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ እንደገለጹት ዜጎች በውጭ ሀገራት ስራ ላይ ሲሰማሩ በእውቀት እና በክህሎት ክፍተት እየተንገላቱ በመሆኑ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ያሉ ሲሆን እንደ መስሪያቤታችን የእውቅና ፍቃድ ስንሰጥም ሆነ ምዘና ስናካሂድ ሙያዊ ስነ-ምግባር በተሞላበት እና የተደራጀ መረጃ በመያዝ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

photo_2024-12-23_00-28-18 photo_2024-12-23_00-28-26

በስልጠናው ላይም የ9ኙም ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪጆች የእውቅና ፍቃድ እድሳት እና የምዘና ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በስልጠናው ላይ ለተነሱ ሃሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡