የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባስልጣን የሙያ ብቃት ምዘና ዘርፍ ታሪካዊ ዳራ
የሀገራችንን ዕድገት ግስጋሴ ለማፋጠን የተነደፈውን የቴክኒክናሙያ ትምህርት ስልጠና ስትራቴጂ መሠረት በማድረግ በ2ዐዐዐ ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣የአስተዳደሩ ካቢኔ ባወጣው ደንብ ቁጥር 1/2000 የልህቀት ማዕከል ተቋቋመ፡፡ይህ የኢንዱስትሪውን የሰለጠነ ሰው ሐይል ፍላጎት ትርጉም ባለው አግባብ ማርካትን ታላሚ አድርጎ የተመሠረተው ማዕከል እስከ 2ዐዐ1 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጥላ ስር ሆኖ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡በ2ዐዐ1ዓ.ም. የከተማው...