All Posts By Super Admin

ሰብአዊ መብትን ያከበረ የኤች አይቪ አገልግሎት ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል አለም አቀፍ የጸረ- ኤች አይ ቪ ቀን በፓናል ውይይት ተከበረ ፡፡

photo_2024-12-10_00-22-21 1

(ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን”ሰብአዊ መብትን ያከበረ የኤች አይቪ አገልግሎት ለሁሉም“በሚል መሪ ቃል 36ኛው የጸረ ኤች አይቪ ቀን የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት በፓናል ውይይት ተከብሯል፡፡ አቶ ስንታሁ ጎሹ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ባለሙያ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በአለም አቀፍ እና በሀገራችን ያለውን የኤች አይቪ አሁናዊ...

ወጣቶችን ያማከለ የጸረ ሙስና ትግል የነገን ስብዕና ይገነባል "በሚል መሪ ቃል አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን በልዩ ልዩ መርሃ ግብር ተከበረ፡፡

photo_2024-12-10_00-09-49 1

ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን"ወጣቶችን ያማከለ የጸረ ሙስና ትግል የነገን ስብዕና ይገነባል"በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ እንዲሁም በአገር አቀፍ ለ 20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የጸረ ሙስና ቀን የባለስልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች አክብረዋል፡፡ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ጋትዌች ቱት በመርሃ ግብሩ ላይ...

በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የክትትልና ቁጥጥር፣የእውቅና ፍቃድ እድሳት፣የድንገተኛ ኢንስፔክሽን እና የሙያ ብቃት ምዘና ግኝት ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት ቀረበ፡፡

photo_2024-12-09_23-57-39 1

ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ፤በስራና ክህሎት ቢሮ የተደረገ የክትትልና ቁጥጥር ሪፖርት፣የእውቅና ፍቃድ እድሳት፣የድንገተኛ ኢንስፔክሽን ግኝት እና የሙያ ብቃት ምዘና ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት ቀረበ፡፡ ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ በመልዕክታቸው እንደገለጹት የበቃ ክህሎት ያለው...

ባለስልጣኑ የተቋማት የእውቅና ፍቃድ እድሳት አፈፃፀም እና የድንገተኛ ኢንስፔክሽን ግኝት ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት አቀረበ፡፡

photo_2024-11-28_09-59-53 1

(ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የተቋማት የእውቅና ፍቃድ አፈፃፀም እና የድንገተኛ ኢንስፔክሽን ግኝት ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት አቀረበ፡፡ አቶ ዳኛው ገብሩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ በመልዕክታቸው የምንሰራው ውድ ሀብት የሆኑት ልጆቻችን ላይ ነው፤ስለዚህ ዘርፉ የሁላችንም ጉዳይ እና የሁላችንንም ትጋት የሚጠይቅ ዘርፍ ነው የትኛውም የህግ ጥሰት ሚታይበት ተቋም...

ባለስልጣኑ የ19 አቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በማሳደስ ርክክብ አደረገ፡፡

photo_2024-11-18_03-39-26 1

ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በከተማው ውስጥ ያሉ የግል የትምህርትና ስልጠና ተቋማትን በማስተባበር በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ለሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖች 19 ቤቶችን በማደስ ርክክብ አከናወነ፡፡ አቶ ዳኛው ገብሩ የትህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ በመርሃ-ግብሩ ላይ እንደተናገሩት በከተማችን ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ...

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጽሑፍ ምዘና ያለፉ መምህራን እና የት/ቤት አመራሮች የማህደረ ተግባር ምዘና እየተሰጣቸው መሆኑን ገለፀ፡፡

photo_2024-11-18_03-33-32 1

ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የኮልፌ ቀራንዮ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ላይ የማህደር ተግባር ምዘናዎች አካሄደ፡፡ የማህደረ ተግባር ምዘናውን ለመመዘን በጀነራል ዋቆ ጉቱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያገኘናቸው መምህርት ወይንሸት እንደተናገሩት የፈተናው ሂደት ጥሩ መሆኑን እና የተደሰቱበት መሆኑን በመግለፅ አቅማቸውን የሚፈትሽና ያላቸውን እውቀት የሚያዳብር መሆኑን ነግረውናል፡፡ እንዲሁም የማህደረ ተግባር...

የመምህራንና የትምህርት አመራሮች የማህደረ ተግባር ምዘና ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

photo_2024-11-18_03-29-01 1

ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የእውቅና ፈቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት ባለፈው በጀት አመት የጹሑፍ ምዘና ወስደው መስፈርቱን ላሟሉ የማህደረ ተግባር ምዘና እየሰጠ መሆኑን ተገልጿል፡፡ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የእውቅና ፈቃድና እድሳት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሮማን በለው በበጀት አመቱ ከተያዘው ተግባር አንዱ የጽሑፍ ምዘናውን ላለፉ መ/ራንና የትምህርት አመራሮች የማህደረ...

ባለስልጣኑ በ2017 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃጸም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡

photo_2024-11-18_03-22-44 1

ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃጸም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡የእቅድ አፈፃፀሙን ያቀረቡት የባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ነብዩ ዳዊት ሲሆኑ በአፈፃፀሙ ላይ እንደተገለጸው በዝግጅት ምዕራፍ ላይ እቅዶችን በማቀድ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ወደ ስራ የተገባ መሆኑን ተናግረዋል፤እንዲሁም...

የጽሑፍ ምዘና ያለፉ መምህራን እና የት/ቤት አመራሮች የማህደረ ተግባር ምዘና እየተሰጣቸው ነው፡፡

photo_2024-11-13_23-12-35 1

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የጉለሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ላይ የማህደር ተግባር ምዘናዎች እያካሄደ መሆኑን የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሸን ባለሙያዎች ተመልከተናል፡፡ በዚህም በፀሐይ ጮራ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ላይ በተገኘንበት ወቅት ምዘናውን ሲያስተባብሩ ያገኘናቸው የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሱፕርቫይዘር የሆኑት አቶ ጌታቸው ታረቀኝ ምዘውን አስመልክቶ እንደገለፁት በምዘናው ላይ የተመደቡት ተመዛኝ መምህራን...

ባለስልጣኑ የተቀናጀ የትምህርት ምዘና እና ቁጥጥር አስተዳደር ስርዓት (IEARMS) ፕሮጀክት ስራው ያለበትን ሂደት ገመገመ፡፡

photo_2024-11-13_23-06-41 1

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ከአልሚ ድርጅት ጋር የተፈራረመውን የተቀናጀ የትምህርት ምዘና እና ቁጥጥር አስተዳደር ስርዓት (IEARMS) ፕሮጀክት ሶፍት ዌር የማበልፀግ ስምምነት ያለበትን የስራ ሂደት የባለስልጣኑ ከፍተኛ ባለስልጣኖች፣ዳይሬክተሮች፣ቡድን መሪዎች እንዲሁም ባለሙያዎች በተገኙበት ገምግሟል፡፡ ባለስልጣኑ የትምህርትና ስልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ፣በስሩ ያሉትን ችግሮችን ለማሻሻልና የአሰራር ስርዓቱን ለማዘመን የሚያግዘው ሶፍትዌር...