የት/ስ/ጥ/ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ የአራዳና ቂርቆስ ቅ/ጽቤት የ2012 የመጀመሪያ ግማሽ አመት እቅድ ክንውኑን ለባለድርሻ አካላትና ለህዝብ ክንፍ እንዲሁም ከቅ/ጽ/ቤቱ አጠቃላይ ሰራተኞች ሪፖርቱን አቅርቧል፡፡ በሪፖርቱ እንደተገልጸው የመማር ማስተማሩን ሂደት በስታንዳርዱ መሰረት እንዳይተገበር ያደረጉ፣ የተማሪ ቁጥር በተጨናነቀ ሁኔታ በመጨመር፣ ግብአቶችን አሟልተው ያልተገኙ፣ በ2011 እውቅና ፈቃድና እድሳት ሲሰራላቸው የነበሩ አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን ግብዓቶችን ያጠፉ፣ እውቅና ፈቃድ ሳይኖራቸው እያስተማሩ...